
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ በአማራ ክልል የሚነሱ የፖለቲካ እና የልማት ጥያቄዎችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት በክልሉ ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል የሕገ መንግሥት፣ የወሰን ይገባኛል እና የሰንደቅ ዓላማ ጉዳዮች በአንድ አካባቢ ወይም ፓርቲ ብቻ የሚፈቱ ሳይኾኑ የሌሎችን ተሳትፎ እና ዘላቂ መፍትሔ የሚሹ ናቸው ነው ያሉት።
እነዚህን ጥያቄዎች በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኩል ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው ምላሽ እንደሚያገኙ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።
በየአካባቢዎች የሚነሱ ለጥያቄዎችን ፈጣን ውሳኔዎችን መስጠት ሌላ ግጭት ሊያስከትል እንደሚችል የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወልቃይት የይገባኛል ጥያቄን በምሳሌነት አንስተዋል።
የሁለቱን ክልሎች ሕዝቦች ያሳተፈ እና በሕገ መንግሥቱ መሠረት በሪፈረንደም ያልተረጋገጠ ውሳኔ ዘላቂ ሰላም እንደማያመጣም ነው ያብራሩት።
አንዱን ወገን ብቻ በማስደሰት ጊዜያዊ እፎይታ መፍጠር የመደመር መንግሥት መርህ እንዳልኾነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለችግሮች ዘላቂ እና አስተማማኝ ሰላም የሚያመጣ ምላሽ መስጠት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
#አሚኮ #ወቅታዊ_ጉዳይ #ጠቅላይ_ሚኒስትር_ዐቢይ_አሕመድ #ባሕር_ዳር #ኢትዮጵያ #AMECO #PMABIYAHMED #PMAbiy #AmharaMediaCorporation #Ethiopia #BahirDar #CurrentNews
✍️ በአድኖ ማርቆስ
#ባሕር_ዳር፡ ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
