“ዘመናዊት ኢትዮጵያን ከሕዝቦች ውሕደትና ትስስር ውጭ ማየት አይቻልም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

16

 

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በዘመናት መካከል በጋብቻ፣ በፖለቲካል ጋብቻ፣ በባሕላዊ ጉዲፈቻ እና በአብሮነት የተሳሰሩ መኾናቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በታሪካችን ውስጥ የሸዋ ሡልጣኔት፣ የኢፋት ሡልጣኔት፣ የጎንደርያን ዘመን፣ የየጁ ዳይናሲቲ እና የዮሪ መኖ መዋቅር የሕዝቦችን ሰፊ መዋሃድ፣ አብሮ መዘመን እና መልማት እንደሚያሳዩ አንስተዋል።

የቅርቡን ዘመን ታሪክ የተመለከተ ሰው ከእነዚህ ሕዝቦች ውሕደት ውጭ ዘመናዊት ኢትዮጵያን ማየት እንደማይችል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “ሚኒልክ ካለ ጎበና፤ ጎበና ካለ ሚኒልክ ዘመናዊት ኢትዮጵያን መፍጠር የሚችሉበት ምንም ዓይነት ዕድል የለም” ብለዋል።

#አሚኮ #ወቅታዊ_ጉዳይ #ጠቅላይ_ሚኒስትር_ዐቢይአሕመድ(ዶ.ር)

#ባሕር_ዳር #ሐምሌ_24_2018_ዓ_ም

✍️ በአድኖ ማርቆስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“የአማራ ሕዝብ በኢትዮጵያ የሕዝብ አንድነት እንዲጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር)
Next article“ብቸኛው ሀገርን የማዳን አማራጭ የመደመር መንገድ መኾኑን ሕዝቡ ተረድቷል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር)