“የአማራ ሕዝብ በኢትዮጵያ የሕዝብ አንድነት እንዲጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር)

17

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ቆይታቸው የአማራ ሕዝብ በኢትዮጵያ ሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የነበረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መኾኑን አስረድተዋል።

የአማራ ሕዝብ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሀገሪቱ የተሻለ የፖለቲካ ሥርዓት እንዲሰፍን፣ ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲኖር እንዲሁም የሕዝቦች አንድነት ይበልጥ እንዲጠናከር አበክሮ የሚሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በየዘመናቱ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ በተደረጉ የተለያዩ የለውጥ ትግሎች ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ኾኖ መቆየቱን እና ለሀገር ግንባታው ከፍተኛ አበርክቶ ማድረጉን አስገንዝበዋል።

#አሚኮ #ወቅታዊ_ጉዳይ #ጠቅላይ_ሚኒስትር_ዐቢይ_አሕመድ #ባሕር_ዳር #ኢትዮጵያ #AMECO #PMABIYAHMED #PMAbiy #AmharaMediaCorporation #Ethiopia #BahirDar #CurrentNews

✍️ በስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“የዘመናችን የሰላም ክተት”
Next article“ዘመናዊት ኢትዮጵያን ከሕዝቦች ውሕደትና ትስስር ውጭ ማየት አይቻልም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)