
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ ከጎንደር ወደ ሁመራ የበረራ አገልግሎት እንደሚሰጥ ለአሚኮ በላከው መግለጫ ጠቁሟል።
የበረራ አገልግሎቱ ዘወትር ቅዳሜ ከጎንደር ወደ ሁመራ የሚደረግ ሲኾን ዘወትር ሰኞ ደግሞ ከሁመራ ወደ ጎንደር አገልግሎት ይሰጣል።
አየር መንገዱ የሀገር ውስጥ በረራ መዳረሻዎችን በማስፋት ሕዝብን ለማገልገል እንደሚሠራ የገለጸ ሲኾን ከጎንደር ሁመራ የተጀመረው አገልግሎትም ማኅበራዊ ግንኙነትን ከፍ የሚያደርግ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
