በክልሉ ለ173 ሺህ ባለይዞታዎች የሁለተኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጥቷል።

14
የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄዱን ቀጥሏል። በጉባኤው ሪፖርት ያቀረቡት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በመሬት አሥተዳደር እና በአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች የተሻሉ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ የገጠር መሬት ይዞታ ዋስትናን የማረጋገጥ፣ የከተማ መሬት ልማት እና አሥተዳደር ሥርዓትን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ ተሠርቷል። የኢንቨስትመንት እና የልማት ተነሺዎች መብት ማስጠበቅ ላይም ትኩረት ያደረጉ ሥራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል።
📌በዚህም ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተሮችን ማከፋፈል፣ የወል እና ሕገ ወጥ መሬቶችን በማስመለስ የተሻለ ውጤት መመዝገቡንም ተናግረዋል። ለአብነትም ለ173 ሺህ 554 ባለይዞታዎች የሁለተኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መስጠት ተችሏል ነው ያሉት።
📌42 ሺህ 409 ባለይዞታዎች የብድር ዋስትና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን አንስተዋል። የመሬት መረጃን በዲጂታል ሥርዓት ለመያዝ በተደረገው ጥረት ሶፍትዌር በማልማት ወደ ዲጂታል ሥርዓት የማስገባት ሥራ መሠራቱንም ጠቁመዋል።
📌 ለ52 ሺህ 423 ባለይዞታዎች እና የልማት ተነሺዎች ከ17 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ካሳ መከፈሉንም ተናግረዋል። በተጨማሪም ለ1 ሺህ 955 ባለይዞታዎች 780 ሄክታር መሬት ትክ የእርሻ መሬት መሠጠቱም ተገልጿል።
✍️በአካባቢ ጥበቃ ልማት ዘርፍ፣ በደን ልማት እና ጥበቃ እንዲሁም የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር በማድረግ በኩልም በስፋት ተሠርቷል ነው ያሉት።
👉 በዚህም ከ46 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ደን መተከሉን ገልጸዋል። 164 ሺህ 961 ሄክታር መሬት እንዲያገግም መደረጉንም አንስተዋል።
👉በከተሞች ማኅበራትን በማደራጀት፣ የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ ክትትል በማድረግ እና የአካባቢን ጽዳት የማረጋገጥ ሥራዎች መሠራታቸውን ነው የተናገሩት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleለአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ የሶማሌ ክልል አስታወቀ።
Next articleየሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስኬታማ ተግባራት ተከናውነዋል።