ለአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ የሶማሌ ክልል አስታወቀ።

15
በሶማሌ ክልል የክረምት የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል።
በአካባቢ ጥበቃና መሬት አስተዳደር ቢሮ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አስተባባሪ መሐመድ ቡሌ ሰመተር እንደገለጹት፤ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን በመትከል የዘርፉን አቅም ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል።
ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብሮች የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመከላከልና የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ተችሏል ብለዋል።
መርሃ ግብሩ የአካባቢን ሥነ-ምህዳር በመጠበቅና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
በዚህም በክልሉ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ ጠቁመው ችግኞቹ ለምግብነት፣ ለአካባቢ ጥበቃና ለእንስሳት መኖነት የሚውሉ መሆናቸውን አንስተዋል።
በክልሉ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ችግኝ ተከላ ተግባር ወጣቶችን፣ ተቋማትንና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
ሕብረተሰቡም በመርሃ ግብሩ እየተተከሉ የሚገኙ ችግኞችን በመንከባከብ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም ገልጸዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በመጪው ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የክልሉ ሕዝብ በንቃት እንዲሳተፍም ጥሪ ቀርቧል፡፡
Previous articleየአማራ ክልልን የንጹህ መጠጥ ውኃ ሽፋን ከ79 በመቶ በላይ ማሳደግ ተችሏል።
Next articleበክልሉ ለ173 ሺህ ባለይዞታዎች የሁለተኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጥቷል።