የአማራ ክልልን የንጹህ መጠጥ ውኃ ሽፋን ከ79 በመቶ በላይ ማሳደግ ተችሏል።

14
የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል። በጉባኤው የ2018 በጀት ዓመት ​አፈጻጸምን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ሪፖርት እያቀረቡ ነው ።
👉የ2018 በጀት ዓመት የንጹህ መጠጥ ውኃ መሠረተ ልማትን በተመለከተ በሪፖርቱ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል፦
✅በገጠር እና በከተማ በተከናወኑ የንጹሕ መጠጥ ውኃ የልማት ሥራዎች 643 ሺህ 850 ሕዝብን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
✅ የክልሉ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ሽፋን ወደ 79 ነጥብ 91 በመቶ አድጓል።
✅ 91 የውኃ ተቋማት ወደ ሶላር ኀይል እንዲሸጋገሩ መደረጉም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
👉የ2018 በጀት ዓመት መሠረተ ልማትን በተመለከተ በሪፖርቱ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል፦
✅በበጀት ዓመቱ የመንገድ ሽፋንን ለማሳደግ በተሠራው ሥራ የዕቅዱን 79 ነጥብ 7 በመቶ ማሳካት ተችሏል።
✅ በሥራውም 2 ነጥብ 58 ቢሊዮን ብር ኅብረተሰቡ ድጋፍ አድርጓል።
✅ የ634 ድልድዮች ጥገና ተጠናቅቋል።
✅59 መናኻሪያዎችም የኢ-ትኬት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ተችሏል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበቅርስ ልማትና ጥበቃ የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።
Next articleለአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ የሶማሌ ክልል አስታወቀ።