በቅርስ ልማትና ጥበቃ የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።

11
በሀረሪ ክልል በቅርስ ልማትና ጥበቃ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የሀረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አፈ-ጉባኤ ሙህየዲን አህመድ ገልጸዋል።
የሀረሪ ብሔራዊ ጉባኤ 6ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። በጉባኤው በሀረሪ ቋንቋና ቅርስ ጥበቃ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የሀረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አፈ-ጉባኤ ሙህየዲን አህመድ በጉባኤው ላይ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ በአለም አቀፉ የጁገል ቅርስ የተከናወኑ የመልሶ ልማት ስራዎች ቅርሱን ለቀጣይ ትውልድ ጠብቆ ለማስተላለፍ የሚያስችሉ ናቸው።
በተለይ ለቅርሱ የተደረገው የመልሶ ልማት አካባቢውን ለኑሮ ምቹ በማድረግ ቅርሱ ሕያውነቱን ጠብቆ እንዲቆይ በማስቻል አበርክቶው የጎላ ነው።
በክልሉ የሀረሪ ቋንቋ፣ባህል፣ቅርስ እና ታሪክ ይበልጥ እንዲያድግና እንዲበለጽግ በማድረግ የተጀመሩ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን በመጠቆም የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
የሀረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም በበኩላቸው የሀረሪ ቋንቋ፣ ባህል፣ ቅርስና ታሪክን ከማልማት፣ከማስተዋወቅና ከመጠበቅ አንጻር የተከናወኑ ተግባራትን በመደገፍ ረገድ ስኬታማ ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።
በተለይ የሀረሪ ቋንቋን ለማሳደግ የክልሉን የቋንቋ ካውንስል ከማጠናከር ጀምሮ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን የሀረሪ ቋንቋ ትምህርት በተመለከተ የክትትልና ድጋፍ ሥራዎችን ማከናወናቸውን ገልፀዋል።
በቀጣይም የሀረሪ ቋንቋን ደረጃ የማሳደግ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና በጁጎል ዓለም አቀፍ ቅርስ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ለመጠበቅ ከወረዳዎች ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ መግለጻቸውን የሀረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
ጉባኤው ሲያካሂደው የነበረውን 6ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት፣2ኛ መደበኛ ጉባኤውን አጠናቋል።
Previous articleከተሞችን በማዘመን በአገልግሎት ሕዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ሥራዎች ተከናውነዋል።
Next articleየአማራ ክልልን የንጹህ መጠጥ ውኃ ሽፋን ከ79 በመቶ በላይ ማሳደግ ተችሏል።