በበጀት ዓመቱ በትምህርት እና በጤና ዘርፍ ውጤታማ ተግባር ተከናውኗል።

8
የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። በጉባኤው የ2018 በጀት ዓመት ​አፈጻጸምን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ሪፖርት እያቀረቡ ነው ።
👉የ2018 በጀት ዓመት የትምህርት አፈጻጸምን በተመለከተ በሪፖርቱ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል፦
🖊በክልሉ የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል የተማሪዎችን ፈተና በስኬት ማጠናቀቅ ተችሏል።
🖊በ12ኛ ክፍል ፈተና ከ59 ሺህ በላይ ተማሪዎች በበይነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናውን ወስደዋል።
🖊በትምህርት ለትውልድ ኢኒሼቲቭ 233 አዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል።
🖊በበጀት ዓመቱ 4 ሚሊዮን 410 ሺህ 954 ተማሪዎች ተመዝግበዋል።
👉የ2018 በጀት ዓመት የጤና አፈጻጸምን በተመለከተ በሪፖርቱ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል፦
የክልሉን ማኅበረሰብ ጤናማ እና አምራች ለማድረግ፤ ተደራሽ እና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመሥጠት በርካታ ሥራዎች መከናወናቸው ተገልጿል።
✅የእናቶች እና ሕጻናት ጤና አጠባበቅን ማሻሻል፤ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልኾኑ በሽታዎችን መከላከል እና በሌሎች ዘርፎችም መሠራቱ ተነስቷል።
✅ የመጀመሪያ ደረጃ የቅድመ ወሊድ ለ872 ሺህ 441 እናቶች እና የአራተኛ ደረጃ ቅድመ ወሊድ አገልግሎት ከ789 ሺህ በላይ ለኾኑ እናቶች ተሰጥቷል።
✅ በወሊድ ወቅት የአተነፋፈስ ችግር ላጋጠማቸው 12 ሺህ 330 ሕጻናትም ድጋፍ ተደርጓል።
✅ ለ821 ሺህ 949 ሕጻናት የኩፍኝ መከላከል ክትባት ተሠጥቷል።
✅ 1 ሚሊዮን 387 ሺህ 155 ለሚኾኑ በወባ ለተጠቁ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሕክምና መስጠት ተችሏል።
✅ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ መድኃኒቶችን እና የሕክምና መሣሪያዎችን ለጤና ተቋማት ማሰራጨት ተችሏል።
✅ በደም ባንኮች 76 ሺህ 498 ዩኒት ደም ተሠብሥቧል።
✅ 4 ሚሊዮን 177 ሺህ 591 የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኀን አባላትን ማፍራት ተችሏል። ከዚህም 6 ቢሊዮን 626 ሚሊዮን 110 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበበጀት ዓመቱ ለ1ሺህ 43 ቅርሶች ጥገና ተከናውኗል።
Next articleከ55 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎት ተጠቃሚ ኾነዋል።