በበጀት ዓመቱ ለ1ሺህ 43 ቅርሶች ጥገና ተከናውኗል።

6
የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል። በጉባኤው የ2018 በጀት ዓመት ​አፈጻጸምን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ሪፖርት እያቀረቡ ነው ።
🚨የ2018 በጀት ዓመት የቱሪዝም ልማትን በተመለከተ በሪፖርቱ ከተነሱ ጉዳዮች መካከልም፦
✅ 250 የቋሚ ቅርሶችን የጉዳት መጠን በደረጃ መለየት ተችሏል።
✅ ለ1ሺህ 43 ቅርሶች ጥገና ተከናውኗል።
✅ 18 የተዘረፉ ቅርሶችን ማስመለስ ተችሏል።
✅ ስድስት የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን በካርታ፤ በጂፒኤስ እና ጎግል ላይ ተደራሽ ማድረግ መቻሉ ተጠቅሷል።
✅ለቱሪዝም መዳረሻዎች 594 ኪሎ ሜትር መንገድ ተሠርቷል።
✅10 ኢኮ-ሎጅ እና ሪዞርቶች፤ 77 ሆቴሎች እና 10 ባሕላዊ ሬስቶራንቶች መገንባታቸው በርእሰ መሥተዳድሩ
ሪፖርት ተነስቷል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ከግብርና ምርት ከ562 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተገኝቷል” አቶ ፈንታው ፈጠነ
Next articleበበጀት ዓመቱ በትምህርት እና በጤና ዘርፍ ውጤታማ ተግባር ተከናውኗል።