“የዛሬው ትጋቴ፤ የነገው ሀገር የማገልገል መሠረቴ ነው”

39

 

በሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ሥር የሚገኘው ተሐድሶ አምባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና 91 በመቶ ታራሚዎችን አሳልፏል።

ትምህርት ቤቱ ላለፉት አራት ዓመታት አንድም ተማሪ ማሳለፍ ያልቻለ ቢኾንም፣ ዘንድሮ ከአንድ ተፈታኝ በስተቀር ሁሉም አልፈዋል። የ7ኛ ክፍል ትምህርቱን በዚሁ ማረሚያ ቤት የጀመረው ታራሚ ከበደ አበባየሁ ተቋሙ ሕይወቱን የሚያንጽበት መልካም አጋጣሚ አድርጎ በመጠቀም ለውጤት እንደበቃ ገልጿል።

“ያለፈው ስህተቴ የትናንት ታሪኬ ነው፤ የዛሬው ትጋቴ ግን ነገ ሀገር የምጠቅምበት መሠረቴ ነው” ብሏል።

ሌላኛዋ ተፈታኝ ነጻነት ታፈሰ ተቋሙ ነገን በብርሃን የምታይበትን አቅም እንደፈጠረላት ገልጻለች።

የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር የቻለሰው አሰፋ እንደገለጹት ፈተናውን እንደ ትልቅ ፕሮጀክት በመውሰድ በፊት የነበሩ የግብዓት ክፍተቶችን ቀድሞ መፍታት ተችሎ እንደነበር አስታውሰዋል።

በተለይም የማጠናከሪያ ትምህርቶችን መስጠት፤ ተደጋጋሚ የመለማመጃ ፈተናዎችን ማሠራት እና የማጣቀሻ መጻሕፍትን ማቅረብ ለውጤቱ መገኘት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል።

#ደብረ_ብርሃን #ነሐሴ_22_2018_ዓ_ም

በደጀኔ በቀለ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article” ውጤቴን ስሰማ በደስታ አልቅሻለሁ” የከፍተኛ ውጤት ባለቤቱ ተመሥገን ሉሌ