“ከሕገወጥ የማዕድን ምርት ቁጥጥር ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ መሠብሠብ ተችሏል” ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ

7
የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው የ2018 በጀት ዓመት ​አፈጻጸምን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ሪፖርት እያቀረቡ ነው። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በበጀት ዓመቱ የክልሉን የማዕድን ሀብት በመለየት፤ ለኢንዱስትሪ ልማት ግብዓት በማዋል እና ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር ረገድ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን አቅርበዋል።
የብረት፤ የኢንዱስትሪ እና የኮንስትራክሽን ማዕድናት ፍለጋ እና ክምችት ማረጋገጥ፤ የአሲዳማ መሬት ማከሚያ የኖራ ማዕድን አቅርቦት፤ የሕገ-ወጥ ማዕድን ቁጥጥር፣ የሥነ-ምህዳር ጥናት እና ካርታ ዝግጅት ሥራዎች መሠራታቸው ተገልጿል።
በ10 ኪሎ ሜትር ስፋት በተደረገ ጥናት 5 ሺህ 148 ቶን የሚገመት የብረት ማዕድን ክምችት ተገኝቷልም ነው ያሉት።
የብረት ፍለጋ እና ክምችት በ20 ካሬ ሜትር ስፋት በላብራቶሪ ውጤቶች ትንተና መሠረት 146 ነጥብ 72 ሜትሪክ ቶን ብረት መገኘቱን ነው ያብራሩት።
ለኮንስትራክሽን ማዕድን ፍለጋ እና አጠቃቀም ሥራ በ440 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ተከናውኖ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ቶን ግራናይት እና 1 ነጥብ 625 ቢሊዮን ቶን ጥቁር ድንጋይ መገኘቱንም አስረድተዋል።
ሕገወጥ የማዕድን ምርት ቁጥጥር ላይ 133 ሺህ 500 በላይ ሜትር ኩብ ሕገ ወጥ ማዕድን መመረቱም ተገልጿል። ከዚህም 27 ሚሊዮን 195 ሺህ 483 ብር ወደ መንግሥት ግምጃ ቤት ማስገባት መቻሉን ነው ርእሰ መሥተዳድሩ የጠቀሱት።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“በክልሉ አበረታች የዕድገት ውጤቶች ተመዝግበዋል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleበአማራ ክልል አምራችአምራች ኢንዱስትሪዎችን በማጠናከር ከ789 ቶን በላይ ተኪ ምርቶች ተመርተዋል።