በሶማሌ ክልል የኑሮ አቅማቸው ዝቅተኛ ለኾኑ ነዋሪዎች የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላለፉ።

14
የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል ሸበሌይ ከተማ የኑሮ አቅማቸው ዝቅተኛ ለኾኑ ነዋሪዎች ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች አስረክቧል።
የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በፋፈን ዞን ሸበሌይ ከተማ ያስገነባቸውን 10 መኖሪያ ቤቶችን ነው ለተጠቃሚዎች ያስረከበው።
በመርሐግብሩ ላይ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ.ር)፣ የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፋ ሙሐመድ፣ እና ሌሎችም የክልሉ መሪዎች እና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
በሸበሌይ ከተማ የኑሮ አቅማቸው ዝቅተኛ ለኾኑ ነዋሪዎች የተገነቡት የመኖሪያ ቤቶች 45 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገባቸው ናቸው። ቤቶቹ መንግሥት የኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ የኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚያከናውነው ጥረቶች አካል መኾኑ ተገልጿል።
በሸበሌይ ከተማ ብቻ በክልሉ መንግሥት እና በፌዴራል ተቋማት የተቀናጀ ጥረት እስካሁን ከ35 በላይ ቤቶች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች መድረሳቸው ነው የተገለጸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከሐምሌ 23 /2018.ዓ.ም ጀምሮ እንደሚያካሂድ ገልጿል።
Next article“የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ሕዝቡ ባደረጉት ተጋድሎ ታጣቂ ጠላቶች እየተመቱ፣ አስታጣቂዎቹም ተስፋ እየቆረጡ ነው” ሌተና ጀነራል መሐመድ ተሰማ