📊በበጀት ዓመቱ ከ240 በላይ ለሚኾኑ ተቋማት የኦዲት ሽፋን ተሰጥቷል።

3

 

🏛️በአማራ ክልል ምክር ቤት የመንግሥት ወጭ አሥተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን ገምግሟል።

የአማራ ክልል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አማረ ብርሃኑ (ዶ.ር) ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት በበጀት አጠቃቀም፣ በኦዲት ሽፋን፣ በኦዲት ጥራት ቁጥጥር እና ማረጋገጥ፣ በተቋማዊ የገጽታ ግንባታ፣ በኦዲት ጥናት እና ምርምር እንዲኹም የኦዲት ውጤታማነትን በማሳደግ የተሻሉ ሥራዎች ተከናውነዋል።

ከፍትሕ፣ ከሚዲያ ተቋማት እና ከቢሮዎች ጋር በኦዲት ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠር እና ተቋማዊ ትስስር የማጠናከር ሥራዎች ተሠርተዋል ነው ያሉት። ባለ ብዙ ዘርፍ ሥራዎችንም የተቋሙ የሥራ አካል በማድረግ ተግባራዊ ማድረጉን አንስተዋል።

👉የኦዲት ሽፋንን የበለጠ ማሳደግ እንደሚገባ፣ የተደረገው ጥረት የኦዲት ተደራጊ መሥሪያ ቤቶችን የውስጥ ኦዲት አቅም ከማጠናከር አንጻር ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ የቋሚ ኮሚቴ አባላት አስተያየት ሰጥተዋል።

👉 ተቋማት የኦዲት ተግባርን የሥራቸው አካል አድርገው እንዲሠሩ በማድረግ እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚገባም ተመላክቷል።

በአማራ ክልል ምክር ቤት የመንግሥት ወጭ አሥተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ እመቤት ከበደ በበጀት ዓመቱ የኦዲት ሽፋንን ለማሳደግ የተደረገው ጥረት የሚበረታታ መኾኑን ተናግረዋል።

👉ሥልጠናዎችን ለባለሙያዎች በመስጠት የኦዲት ጥራት እንዲሻሻል የተደረገው ጥረት እና የዲጂታላይዜሽን አሠራርን መተግበሩ የሚበረታታ ነውም ብለዋል።

👉የኦዲት ሽፋንን ለማሳደግ በተያዘው ዕቅድ መሠረት በፋይናንስ እና ሕጋዊነት ኦዲት ላይ ከ240 በላይ ተቋማትን ኦዲት ማድረግ መቻሉ በጥንካሬ የተገመገመ መኾኑን አስረድተዋል።

👉በተቋሙ የሚስተዋሉ አሠራሮችን በመፈተሽ እስከ ታች ድረስ ለማስተካከል የተደረገው ጥረትም የተሻለ እንደነበር ጠቁመዋል።

👉 ለልዩ ኦዲት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት፣ የኦዲት አገልግሎት ሽፋንን የበለጠ ማሳደግ እንደሚገባም የቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢዋ አስገንዝበዋል።

👉የከፋ ኦዲት ግኝት ያለባቸውን ተቋማት እርምጃ አወሳሰድ ላይ ጠንካራ ሥራ መሥራት፣ ከአጋር አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር እና የክዋኔ ኦዲት ተግባርን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።

#አሚኮ​ #AmharaRegion #AuditReport

#ባሕር_ዳር #ሐምሌ_22_2018_ዓ_ም

✍️ዘጋቢ:-አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article🌿መትከል ብቻ ግብ አይደለም፤ ለፍሬ ማብቃት ያስፈልጋል።🍎🍌
Next articleኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ 607 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ አግኝታለች። 🇪🇹