ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ!

4

 

ባሕር ዳር: ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዘመኑ ​የዲጂታል ዓለም ነው። ይህም የማኅበረሰቡን የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ከመቼውም ጊዜ በላይ ፈጣን እና ቀላል አድርጎታል።

በእጅ ባለ ስልክ ብቻ የገንዘብ ዝውውር ማከናወን፣ ግብይቶችን መፈጸም እና የተለያዩ አገልግሎቶችን ማግኘት የተለመደ ተግባር ኾኗል።

​ነገር ግን የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሌላው ደክሞ ያፈራውን ሃብት ለመመዝበር የሚያደቡ አጭበርባሪዎች በዝተዋል።

ባንኮች በየጊዜው ለደንበኞቻቸው የሚያስተላልፏቸው የጥንቃቄ መልዕክቶች የዚህ ማሳያ ናቸው።

​ስለዚህ በተለይ የገንዘብ ዝውውር እና ግብይትን በዲጂታል አገልግሎት ስንጠቀም ጥንቃቄ ማድረግ ይኾናል።

መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች፦

✍️ጓደኛ ወይም ዘመድ በመምሰል በማኅበራዊ ሚዲያ የሚላኩ መልዕክቶች የገንዘብ ዝውውር ክፍያ ከመፈፀም በፊት የመልዕክቱን ትክክለኛነት ማረጋገጥ፤

✍️ምስጢራዊ ቁጥርን ለራስ ብቻ መያዝ፦
የይለፍ ቃልን (PIN) እና የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል (OTPs) ለሌሎች አለማጋራት፤ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ሲጠቀሙ የማያውቋቸውን ሰዎች እንዲያግዙ ከመጠየቅ ይልቅ ቅርብ ወደ ኾነ የባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ እገዛ ማግኘት፤

✍️ትክክለኛውን መተግበሪያ ብቻ መጠቀም፦
የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያን ከፕሌይስቶር እና አፕስቶር (PlayStore & AppStore) ብቻ ማውረድ፣ የስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና የባንክ መተግበሪያውን በየጊዜው ማዘመን ያስፈልጋል።

✍️ለተጨማሪ ደህንነት ጠንካራ የይለፍ ቃሎችን እና የባዮሜትሪክ ማረጋገጫን (የጣት አሻራ ወይም የፊት ለይቶ ማወቂያ) መተግበር፤

✍️ስልክ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ማመልከት፤ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶችን ማቋረጥ፤

✍️የሒሳብ እንቅስቃሴን በየጊዜው መከታተል፤ ማንኛውም የማጭበርበር ሙከራ ካጋጠመ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ማነጋገር ወይም ወደ ባንክ ደንበኞች የጥሪ ማዕከል መደወል ያስፈልጋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልእክት፦