
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ የማይበገር የጤና ሥርዓት ለመገንባት ከቢሮው እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ የተሠራው ሥራ ውጤታማ እንደነበር ገልጸዋል።
ተግባርን አቀናጅቶ በመምራት፣ የተደራጀ ክትትል እና የድጋፍ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ፣ ሞዴል የጤና ተቋማትን በመፍጠር፣ ኅብረተሰቡን ያሳተፈ የጤና አገልግሎት ሥርዓቶች ውጤታማ መኾናቸውን ገልጸዋል።
በ2018 በጀት ዓመት የተገኙ ተሞክሮዎችን በማስፋት ክፍተቶችን አርሞ በ2019 በጀት ዓመት የተሻለ ለመፈጸም መዘጋጀት እንደሚገባም አሳስበዋል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ኀላፊ ሰኢድ የሻው 27 የሚኾኑ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የከተማ አሥተዳደሩን ጤና ጣብያዎች ደረጃ ለማሻሻል ጥረት መደረጉን አንስተዋል።
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ኀላፊ የሽዋስ አንዱዓለም በ84 ጤና ጣቢያዎች መሳሪያ በማሟላት የአልትራ ሳውንድ ምርመራ አገልግሎት መስጠት መቻሉን አንስተዋል።
በሁሉም ወረዳዎች ላይ የማኅበረሰብ አቀፍ መድኃኒት ቤቶችን ለማስፋፋት ታቅዶ በ15 ወረዳዎች ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል። በቀጣይም በጤና ተቋማት የዲጂታላይዜሽን ሥርዓትን ተገባራዊ ለማድረግ ትኩረት እንደሚሰጥም ጠቁመዋል።

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
