የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ የላቀ የማዕከላዊ ላበራቶሪ ሥራን አስጀመረ።

10

 

የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የሳይበር ደኅንነት፤ የሰው ሠራሽ አስተውሎት፤ የአውቶሜሽን፣ የኮሙዩኒኬሽን እና ኤሌክትሮኒክስ ዘርፎች ምርምር የሚካሄድበት ላቦራቶሪ አስመርቋል።

ላበራቶሪው የተለያዩ ባለሙያዎች ሠልጥነው ብቁ የሚኾኑበትም ነው።

በላበራቶሪው ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ ላበራቶሪው የመከላከያ ተቋምን በቴክኖሎጅ ለማሳደግ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል።

ላበራቶሪው ከመከላከያ ተቋማት በተጨማሪ የሲቪል ተቋማትን በቴክኖሎጅ ለማስታጠቅ እና ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት ያስችላል ብለዋል።

የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ የላቀ የላበራቶሪ ማዕከል ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት እና ተወዳዳሪ የቴክኖሎጅ ባለቤት ለመኾን የሚያስችል ማዕከል መኾኑንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

#Ameco #ኢትዮጵያ🇪🇹 #DefenceUniversity
#ባሕር_ዳር #ሐምሌ_19_2018 ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ተመስገን ዳረጎት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየበረሃውን ጉዞ ያስቆመው አረንጓዴ ግንብ፤ የቻይና ተሞክሮ እና የኢትዮጵያ “አረንጓዴ ዐሻራ”