የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጽንፈኞች የዘረፏቸውን የሕጻናት አልሚ ምግቦች እና ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር አዋለ።

3

 

በቢቡኝ ወረዳ ጮቄ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛ ቡድን በመጋቢት 2018 ዓ.ም የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለቅድመ መደበኛ ተማሪዎች የላከውን 120 ኩንታል አልሚ ምግብ ዘርፎ ለታጣቂው ሊመግብ ቆይቷል። ቡድኑ የህጻናቱን አልሚ ምግብ በሰዴ ወረዳ በግ መሸጫ በተባለ ስፍራ በግለሰብ ቤት ካከማቸበት ቦታ ከሰሞኑ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ባደረገው አሰሳ እና ፍተሻ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የ6ኛ ዕዝ ወልወል ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ዓለምሰገድ ተስፋዬ ገልጸዋል።

ኮሎኔል ዓለምሰገድ እንዳሉት የአካባቢውን ሰላም ለማደፍረስ እና የሕዝብን ስቃይ ለማባባስ ሲንቀሳቀስ የነበረው ጽንፈኛ ቡድን የነገ ሀገር ተረካቢ የኾኑ ሕጻናትን ለርሀብ እና ለችግር ለመዳረግ ያደረገውን አስነዋሪ ተግባር ከሽፏል። 120 ኩንታል ዓልሚ ምግብ የተያዘ ሲኾን ለወረዳው አስረክበናል ስለመረከቡም ገልጸዋል።

ጽንፈኛ ቡድኑ ለሎጀስቲክስ እና ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች በክፍለ ጦሩ እጅ መግባታቸውንም አንስተዋል።

አሁን ላይ ጽንፈኛ ቡድኑ የመጨረሻ ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ገብቷል ያሉት አዛዡ ሠራዊቱ በሚወስደው የማያዳግም እርምጃ እየተበታተነ እና ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ እየደረሠበት መኾኑን ነው የገለጹት።

መረጃው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ነው።

#AMECO #EthiopianDefenseForce
#ባሕር_ዳር #ሐምሌ_19_2018 ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article🌱 አረንጓዴ አሻራ፤ ከችግኝ ተከላ ዘመቻነት ወደ ዘላቂ የኢኮኖሚ እና የሥነ-ምሕዳር ግንባታ!
Next articleየመደጋገፍ እና የወንድማማችነት እሴት፤ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀረሪ ክልል።