
76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በሀገሪቱ የተመዘገቡ የዘርፉን ዓበይት ስኬቶች በጉባኤው መክፈቻ ላይ አብራርተዋል። ሚኒስትሯ በተለይም በእናቶች፣ በሕጻናት እና በጨቅላ ሕጻናት ሞት ቅነሳ ላይ የተመዘገቡ አዎንታዊ ውጤቶችን አንስተዋል።
የእናቶች እና ከ5 ዓመት በታች ሕጻናት ሞት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ያነሱት ሚኒስትሯ የኅብረተሰብ አቀፍ የጤና መድኅን ሚሊዮኖችን ተጠቃሚ ማድረጉን ተናግረዋል።
የመሠረታዊ ጤና አገልግሎት ተደራሽነት፣ የወሊድ ክትትል አገልግሎት ሽፋን፣ በመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ እና ተዳራሽነት ላይ የተከናወኑ ሰፊ ተግባራትን አንስተዋል።
የጤና ባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ ዕድገቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። የአንድ ሀገር የጤና ደኅንነት ከራሱ ቁጥጥር ውጭ ባሉ የውጭ ሀገራት የአቅርቦት ሰንሰለቶች ላይ ብቻ መደገፍ እንደሌለበት አብራርተዋል።
ለሀገሪቱ የጤና ዕድገቶች እና ለስኬቶቹ ዲጂታል ቴክኖሎጂ እያገዘ መኾኑን እና እንደ አህጉርም ለዘላቂ ዕድገት ቴክኖሎጂን ማዘመን እንደሚገባ አንስተዋል።
የጤናው ዘርፍ ችግሮችን እና ወረርሽኞችን የሚቋቋም እንዲኾን ትብብር ተገቢ መኾኑን አስገንዝበዋል፡፡
#አሚኮ #ጤና #ኢትዮጵያ 🇪🇹
#አዲስ_አበባ #ነሐሴ_19_2018_ዓ_ም
ዘጋቢ: መሰረት መቅጫ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
