የአካባቢ ጥበቃ ዋና የመንግሥት ትኩረት ነው።

10

 

የአካባቢ ጥበቃ ተግባራት ከሀገራዊ ፕሮጀክቶች ጋር ተጣጥመው እየተሠሩ መኾናቸውን የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል።

የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሊሴ ነሜ (ዶ.ር) የአካባቢ ንጽሕናን የሚጠብቅ እና ቆሻሻን የሚጸየፍ ትውልድ መፍጠር ትውልድን ማዳን ነው ብለዋል።

የአካባቢ ብክለትን የሚያስከትሉ ችግሮችን ለመፍታት ባለፉት ዓመታት የሕግ ማሻሻያዎች ተደርገው ተፈጻሚ መኾናቸውን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ ባለፉት አራት ዓመታት ከአራት አዋጆች በላይ ተሻሽለው ሥራ ላይ መዋላቸውን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ፤ በኮሪደር ልማት እና በአካባቢ ጥበቃ በሠራችው ተግባር የኮፕ 32 ጉባኤ አዘጋጅ ኾና እንድትመረጥ አስችሏታል ነው ያሉት።

እንደ ሀገር የብክለት መጠንን ይበልጥ ለመቀነስ የላስቲክ ከረጢቶች አጠቃቀምን መቆጣጠር፤ የአደገኛ ቆሻሻዎች አያያዝን ማሻሻል እና የድምጽ ብክለትን መከላከል ላይ ያተኮሩ የቁጥጥር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ማኅበረሰቡ ለአካባቢ ጥበቃ እያደረገ ያለው ተሳትፎ የሚበረታታ በመኾኑ የሠለጠነ ማኅበረሰብ በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሁላችንም አይተኬ ሚና አለን ነው ያሉት።

“ጽዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ” የሚለውን ንቅናቄ መሠረት በማድረግ ለትውልድ የምትመች ኢትዮጵያን በጋራ እንገንባ ብለዋል።

#ameco #EnvironmentEthiopia
#አዲስ_አበባ_ሐምሌ_18_2018ዓ_ም

ዘጋቢ፦ አየለ መስፍን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ተሳታፊዎች የምክክር ተሳትፏቸው በመከባበር እና በመደማመጥ ላይ የተመሠረተ ነው” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ