“ቆሻሻን ተጠይፎ የሚያስወግድ ትውልድ ተፈጥሯል” ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ

8

 

ጽዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ” በሚል መሪ መልዕክት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የፕላስቲክ፣ አደገኛ ቆሻሻ እና የድምጽ ብክለት መከላከል ንቅናቄ ማሥጀመሪያ መርሐግብር አካሂዷል።

ባለፉት ስድስት ወራት የተደረገውን ሀገር አቀፍ የንቅናቄ መድረክ መሠረት በማድረግ ከ5 ሚሊዮን በላይ ለሚኾኑ የኅብረተሰብ ክፍል የአካባቢ ንጽህና እና የድምጽ ብክለት ግንዛቤ እንዲያገኙ መደረጉን ያነሱት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ኀላፊ እሸቱ ለማ (ዶ.ር) ናቸው።

የድምጽ ብክለት በሚያደርሱ ተቋማት ላይ የእርምት እርምጃ ተወስዷል በዚህም የብክለት ምጣኔ መቀነስ ችለናል ነው ያሉት።

በዚህ ዓመትም የሦሥተኛው ዙር የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ መድረክ ተፈጥሯል፤ በአካባቢ ጥበቃ ሥራ አዲስ አበባ ከዓለማችን ጽዱ ከተሞች 16ኛ ደረጃን ይዛ ተመዝግባለች ይህን ለውጥ ማስቀጠል ይገባልም ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኀላፊ ጃንጥራር ዓባይ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ልማት የሚረጋገጠው የአካባቢ ጥበቃ ሲረጋገጥ ነው ብለዋል።

የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄን እውን የምናደርገው የተሠራውን በመከታተል እና በመጠበቅ ነው፤ የምንሠራቸው የልማት ሥራዎች ሁሉ የአካባቢ ጥበቃን መሠረት ያደረጉ መኾን አለባቸም ብለዋል።

አዲስ አበባ ከተማ ከምንም ተነስታ 43 የሚጠጉ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ማዕከል ገንብታለች፣ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በማላቅ የከተማዋን ልማት እናረጋግጣለንም ነው ያሉት።

በመርሐግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ሐምሌ ወርን ጨምሮ የሦሥት ወር የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራሞችን ይፋ ያደረገ ሲኾን ይህም፦

📌 ሐምሌ ወር/2018 ዓ.ም የፕላስቲክ ብክለት መከላከል ሥራ

📌 ነሐሴ ወር/2018 ዓ.ም አደገኛ ቆሻሻን መከላከል ሥራ

📌 መስከረም ወር/2019 ዓ.ም የድምጽ ብክለት መከላከል ሥራ እንደሚሠራ ተጠቁሟል።

#አሚኮ #CleanEthiopia #Addisababa

#አዲስ_አበባ፡ ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም

ዘጋቢ: አየለ መስፍን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article🚨 ሰላምን በማደናቀፍ እና በተከበብኩኝ ትርክት ሕልውናን በሕዝብ ደም የማቆየት የሕገ ወጡ ሕወሃት አባዜ 🩸🛑
Next article“ተሳታፊዎች የምክክር ተሳትፏቸው በመከባበር እና በመደማመጥ ላይ የተመሠረተ ነው” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ