
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለ6 ወራት በሠለጠኑ የመጀመሪያዎቹ የኤአይ ስታርትአፕ ሠልጣኞች ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል። የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሀገራዊ ራዕይ እና ጥረት ፍሬዎችን ማየት ተጀምሯል ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ለዘርፉ የሰጠዉ ልዩ ትኩረት እና ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ባስቀመጠዉ ግልጽ አቅጣጫ ይህ ማዕከል ዕውን እንዲሆን አበርክቶው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ዘርፉን ለማሳደግ ለሰጡት አመራርም ምስጋና አቅርበዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለኤአይ ስታርታፕ ማዕከል የቴክኒክ ሥልጠና፣ የምርት ልማት ክህሎት እንዲሁም የገበያ ስትራቴጂ ሥልጠናዎችን በስፋት እና በዓይነት በተደራጀ መልኩ መሰጠቱን ተናግረዋል።
ማዕከሉ ለስታርትአፖቹ ካቀረበው ሥልጠና ባለፈ ምቹ የሥራ ቦታ፣ ደረጃውን የጠበቀ የኤአይ ወርክሾፕ፣ የክላውድ ዳታ ሴንተር እና ከፍተኛ የኮምፒዩቲሽናል ሪሶርስ ተጠቃሚ አድርጓቸዋል ብለዋል።
በተጨማሪም ሜንተርሺፕ በመስጠት እና ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ኮንፈረንሶች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ በኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ የኤአይ ተመራማሪዎች የቅርብ ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ መደረጉን ገልጸዋል።
ድጋፉ ወጣቶቻችን ተሰጥዖዓቸውን ወደ ትልቅ እድል የሚቀይሩበት ምቹ መስክ ፈጥሮላቸዋል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እናንተ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ አምባሳደሮች ናችሁ፣ ለኢትዮጵያ የላቀ የቴክኖሎጂ ጉዞ ልትተጉ ይገባል ብለዋል።
#ባሕርዳር #ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም
#አሚኮ #digitatethiopia #Ethiopia
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
