ጤናማ ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚያስችሉ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።

6

 

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ እያካሄደ ነው።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን በማረጋገጥ ጤናማ የኾነ ማኅበረሰብ ለመገንባት በቁርጠኝነት እየተሠራ ነው ብለዋል።

በየደረጃው ላለው የጤና አመራር ሥልጠናዎችን በመስጠት በዕውቀት ላይ የተመሠረተ የጤና አመራር እንዲያዳብሩ እየተደረገ ነው። ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናዎችን ለጤና ባለሙያዎች በመስጠት በኩልም በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

ዘላቂ የጤና ፋይናንስ ሥርዓትን ለመገንባት ራስን ለመቻል የተጀመረው ጥረት በበጀት ዓመቱ አበረታች ሥራዎች ተሠርተዋል ነው ያሉት። የጤና ተቋማት በሚሠበሥቡት ገቢ እና በጤና መድኅን አሠባሠብ ተስፋ ሰጭ ለውጥ መምጣቱንም ገልጸዋል።

የሕክምና ግብዓቶችን በማሻሻል በኩል ትላልቅ የሕክምና መሳሪያዎች በጤና ጣቢያዎች ደረጃ ለማቅረብ የተጀመሩት ሥራዎችም የሚበረታቱ ናቸው ብለዋል።

የማኅበረሰብ አቀፍ መድኃኒት ቤቶችን ለማስፋፋት እየተደረገ ባለው ተግባር በየወረዳዎች በርካታ የማኅበረሰብ መድኃኒት ቤቶች መገንባታቸውንም ጠቁመዋል።

የጤና መረጃ ሥርዓትን ዘመናዊ እና ዲጂታል በማድረግ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የተለያዩ ሲስተሞችን በማልማት የተጀመረው አሠራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የጤና አገልግሎት ፍትሐዊነት እና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በርካታ የጤና ተቋማት ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውንም አንስተዋል።

በ2019 በጀት ዓመት የተጀመሩትን በማጠናቀቅ አዳዲስ የጤና መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለመጀመር ትኩረት እንደሚደረግ አመላክተዋል።

የተገኙ ተሞክሮዎችን በመቀመር፣ ጉድለቶችን በማረም እና ችግሮችን ወደ ዕድል በመቀየር ለትውልድ የሚዘልቅ ሥራን መሥራት በየደረጃው ካለው የዘርፉ መሪ እና ባለሙያ እንደሚጠበቅም አስገንዝበዋል።

#AMECO #AmharaHealthBureau #Health #HealthyCommunity

#ባሕር_ዳር፡ ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየታየው እና የተሰማው ሁሉ አይታመንም!
Next article” ጽናት ፤ ታሪካዊ መጽሐፍ ብቻ ሳይኾን ውርስ ነው” ፕሮፌሰር መንገሻ አድማሱ