“ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከሚሠሩ ታሪካዊ ጠላቶቻችንን ጋር በጋራ አንሠራም” የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች

26

 

በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።

የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች የሕዝባችን ስቃይ እና እንግልት በመረዳት ሰላምን መርጠናል ብለዋል።

ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከሚሠሩ ታሪካዊ ጠላቶቻችንን ጋር በጋራ አንሠራም ነው ያሉት። በግጭት የባከነውን ጊዜ በልማት ለማካካስ ከመንግሥት ጎን በመኾን እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

ከፎገራ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሕዝባቸውን ለመካስ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

#የሰላምአማራጭ_ለዘላቂሰላም

#ባሕር_ዳር፡ ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“🌊⚖️የዓባይ ፍትሕ፤ የግድቡ እውነት እና የካይሮ ፍርሃት
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከጋና ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ጋር ተወያዩ።