
በዚህም መሠረት በ8ቱ ምርጫ ክልሎች ለሚያስፈጽመው የ7ኛው ዙር ቀሪ ምርጫ ለመራጮች ምዝገባ እና ለድምፅ መስጫው ዕለት በሁሉም ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎችን ገለልተኝነታቸውንና መሥፈርቱን ማማላታቸውን አረጋግጦ በጊዜያዊነት ለመቅጠር እንደሚፈልግ ቦርዱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አመልክቷል።
በመሆኑም መሥፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች ተከታዩን ማስፈንጠሪያ https://nebe-election.org/recruitment በመጠቀም ከዛሬ ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ማመልከት እንደሚችሉ ገልጿል።
የምልመላ መሥፈርት፡-
• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦ 12ኛ እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የሥራ ቦታ፦ ቦርዱ ባቋቋማቸው የምርጫ ጣቢያዎች፣
• የክልሉን የሥራ ቋንቋ መናገር እና መጻፍ የሚችል/ምትችል፣
(ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ)
