
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ምሥራቅ ዕዝ ስር የሚገኙ ክፍለ ጦሮች በሰሜን ወሎ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ባካሄዷቸው የተቀናጁ ዘመቻዎች በጽንፈኛው ቡድን ላይ ድል መቀዳጀታቸውን አስታውቋል።
በጉባላፍቶ ወረዳ እና አካባቢው የተካሄደውን ዘመቻ የመሩት የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ሽፈራው ምናሉ በተወሰደው የተጠና ዘመቻ በጽንፈኛው ቡድን ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን ገልጸዋል።
በስፍራው የነበሩ ታጣቂዎች ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውን ጠቁመው የተለያዩ የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች፣ ጀኔሬተር እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች መማረካቸውን አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል በላስታ ወረዳ የሚገኝ ክፍለ ጦር ባካሄደው ዘመቻ የጽንፈኛውን ቡድን በማጽዳት የአካባቢውን ሰላም ማረጋገጥ መቻሉን የ61ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል መለስ አሻግሬ ተናግረዋል። አዛዡ በተወሰደው እርምጃ የተለያዩ መሳሪያዎች እና ተተኳሾች መያዛቸውን ገልጸዋል።
የክፍለ ጦር አዛዦቹ በዘመቻው ለተገኘው ውጤት የአካባቢው ኅብረተሰብ ያደረገው ከፍተኛ ትብብር እና ድጋፍ የሚመሰገን መኾኑን ጠቅሰው ይህ አጋርነት እና ትብብር በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ነው።
#አሚኮ #መከላከያሠራዊት #ኢትዮጵያ
#ባሕር_ዳር፡ ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
