
ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ቁልፍ መሰረተ ልማትን የሚያሥተዳድሩ እንደ መብራት፣ የውኃ፣ የቴሌኮም፣ የፋይናንስ ተቋማት የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነው።
አጥቂዎች ደካማ የይለፍ ቃላትን እና ዘመናዊ ያልኾኑ ሶፍትዌሮችን እንደ ክፍተት በመጠቀም ወደ ሲስተም በመግባት መረጃዎችን አግተው ይይዛሉ፤ ወይም የገንዘብ ማጭበርበር ይፈጽማሉ።
1.አራቱ መሠረታዊ ጥንቃቄዎች
•ሠራተኞችን ማሠልጠን፦ ሠራተኞች አጠራጣሪ ኢ-ሜይሎችን፣ መልዕክቶችን እና ሊንኮችን (Phishing) ለይተው እንዲያውቁና ሪፖርት እንዲያደርጉ ሥልጠና መስጠት።
•ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም፦ በቀላሉ የማይገመቱ፣ ቁጥር፣ ፈደላትና ምልክቶችን የያዙ የይለፍ ቃላትን መጠቀምን በተቋም ደረጃ ግዴታ ማድረግ።
•ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ (MFA) መጠቀም፦ ከይለፍ ቃል በተጨማሪ ሁለተኛ ደረጃ ማረጋገጫ (2-Factor Authentication) በመጠቀም የመለያዎችዎን ደህንነት ማጠናከር።
•ሶፍትዌሮችን ማዘመን (Update)፦ የደህንነት ክፍተቶችን ለመድፈን የሲስተምና የሶፍትዌር ማሻሻያዎችን (Security Patches) ወዲያውኑ መጫን።
2.የደህንነት አቅምን ማሳደግ
•የሲስተም እንቅስቃሴን መከታተል (Logging)፦ ያልተለመዱና አጠራጣሪ የሲስተም እንቅስቃሴዎችን ለመለየት ቁጥጥር ማድረግ።
•የመረጃን ቀሪ/ምትክ ማስቀመጥ (Backup)፦ የድርጅቱን ወሳኝ መረጃዎች በየጊዜው ምትክ መያዝ፤ ይህም ጥቃት ቢከሰት እንኳ በፍጥነት ወደ መደበኛ ሥራ ለመመለስ ይረዳል።
•መረጃን በምስጢር መቆለፍ (Encryption)፦ የመረጃ ቋቶችንና መሣሪያዎችን በምስጢር በመቆለፍ መረጃዎች አጥቂዎች እጅ ቢወድቁ እንኳ እንዳይነበቡ ማድረግ።
3.የሳይበር ደህንነት ባሕልን መገንባት
•የአመራር ቁርጠኝነት፦ የድርጅት መሪዎች ለሳይበር ደህንነት ቅድሚያ መስጠትና የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎችንና ኃላፊዎችን በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ማሳተፍ።
•የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ዕቅድ (Incident Response Plan) ማዘጋጀት፦ ጥቃት ቢከሰት የድርጅቱ ሥራ እንዳይቋረጥ የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን አስቀድሞ ማቀድና መለማመድ።
•ጥቃቶችን ሪፖርት ማድረግ፦
አጠራጣሪ ኹኔታዎች ወይም ጥቃቶች ሲያጋጥሙ ወዲያውኑ ለሚመለከታቸው ክፍሎች እና ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አሥተዳደር ሪፖርት የማድረግን ኢመደአ ይመክራል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
