
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የምርት እና ግብይት፣ የገበያ አረጋጊ፣ የፀረ ኮንትሮባንድ እና ሕገወጥ ንግድ ቁጥጥር ጥምር ግብረ ኀይል የቴክኒክ ኮሚቴ የ12 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም እየገመገመ ነው።
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኀላፊ እና የግብረኀይሉ ቴክኒክ ኮሚቴ ሠብሣቢ አያሌው አባተ (ዶ.ር) የኢኮኖሚ ወንጀሎች በዋናነት የፖለቲካ አለመረጋጋት ከማምጣት ጀምሮ ውሥብሥብ የኾነ ማኅበራዊ ቀውስ ውስጥ እያስገቡ ስለኾነ በጉዳዩ ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት አስፈላጊ እንደነበረ ተናግረዋል።
ለዚህም የሸማቹን ማኅበረሰብ ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል የግብረኀይል አደረጃጀቱን የፌዴራል ተቋማት ባሉበት በመመሥረት ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል።
በዚህም የሸማቹን ማኅበረሰብ ደኅንነት እና ጤንነት ለመጠበቅ ግብረኀይሉ ትልቅ አስተዋጽኦ ሲያበረክት መቆየቱን ገልጸዋል።
ብዙ ጊዜ በንግድ ዘርፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የሀገሪቱን እሴት እና ባሕል የሚያጠፉ ናቸው ያሉት ምክትል ቢሮ ኀላፊው በሀገሪቱ እና በትውልዱ ላይ ትልቅ ጉዳት የሚያደርሱ መኾናቸውን ነው የተናገሩት።
ከዚህ አኳያም አደረጃጀቱ ተጠናክሮ ምላሽ ለመስጠት ሞክሯል ነው ያሉት። ሢሠሩ የቆዩ ሥራዎችም ዛሬ ተጠቃለው እንደሚገመገሙ ነው ያመላከቱ።
በግምገማው የተገኙ ግብዓቶች ለቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ በመነሻነት የሚያገለግሉ ይኾናልም ብለዋል።
#ባሕር_ዳር ሐምሌ 09/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
