በበጀት ዓመቱ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ፓስፖርቶችን ለዜጎች ማሰራጨት መቻሉን የኢትዮጵያ ኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አስታወቀ።

1
የኢትዮጵያ ኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ዐበይት ተግባራት እና ያስመዘገባቸውን ስኬቶች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጠት የኢትዮጵያ ኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት
በበጀት ዓመቱ 1ነጥብ 6 ሚሊዮን ፓስፖርቶችን ለዜጎች ማሰራጨት መቻሉን ገልጸዋል።
📊 የቤተሰብ ምዝገባ፦ በሲቪል ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት 6 ሚሊዮን ዜጎችን መመዝገብ ተችሏል።
🤖 ዘመናዊ አሠራር፦ የምዝገባ ሥርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሲስተም በማበልፀግ ሥራ ላይ ውሏል።
✈️ የመንገደኞች መስተንግዶ፦ በአየር እና በየብስ ድንበር 7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ገቢ እና ወጭ መንገደኞች ተስተናግደዋል።
💰 የገቢ አሠባሠብ፦ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 42 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሠብሥቧል። ከዚህ ውስጥ 5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብሩ በቆንስላ ከሚሰጡ አገልግሎቶች የተገኘ ነው።
🚫 የሕግ ማስከበር ሥራ፦ 4ሺህ 883 የውጭ እና የሀገር ውስጥ ዜጎች በተጭበረበረ ሰነድ አገልግሎት ለማግኘት ሲሞክሩ ተደርሶባቸዋል።
55 ሺህ የሚኾኑ ዜጎች በሕገ ወጥ መንገድ ሊወጡ እና ሊገቡ ሲሉ ተይዘው ሕጋዊ እርምጃም ተወስዶባቸዋል።
⚠️ የአገልግሎቱ ማሳሰቢያ፦ዜጎች ወደ ኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሲመጡ ሕጋዊ እና አስፈላጊ የኾኑ ሰነዶችን ብቻ ይዘው መምጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
#አዲስ_አበባ፡ ሐምሌ 9/2018 ዓ.ም
✍️ ዘጋቢ፦ ሰላማዊት ነጋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየሸማቹን ማኅበረሰብ ደኅንነት እና ጤንነት የሚጠብቁ ሥራዎች ተሠርተዋል።
Next articleየሐረር ከተማ የኮሪደር ልማት፤ የመሠረተ ልማት ሽግግር እና የወደፊት ተስፋ