🚨 ሕገወጡ ሕወሃት ሰላም እና መረጋጋት እንዳይመጣ እንቅፋት የሚፈጥር የጥፋት ኃይል ነው።

51

 

ከጽንሰቱ ጀምሮ ጦርነት፣ ግጭት እና በዘር መከፋፈል የማንነት መገለጫዎቹ ናቸው፤ ሕገ ወጡ የሕወሃት ቡድን። ይህ ቡድን ብሔር ተኮር እሳቤን በማራመድ፤ የሀገርን ሃብት በመዝረፍ እና ንጹሐንን በግፍ በመጨፍጨፍ ይታወቃል።

የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማኅበር ዋና ሥራ አሥኪያጅ ዶክተር ገሠሠው ወንድም ሕወሃት በ27 ዓመት ቆይታው በወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ሕዝብ ላይ በደል ሲፈጽም እንደነበር አንስተዋል።

📌ሕገ ወጡ ሕወሃት በሥልጣን ዘመኑ በወልቃይት ሕዝብ ላይ ምን በደል ፈጸመ?

​📢 በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል። የሃይማኖት አባቶች እና ታሪክ አዋቂዎች እንዲገደሉ አድርጓል ብለዋል።
​
📢 በሺህዎች የሚቆጠሩ የሁመራ አካባቢ ተወላጆች ወደ ሱዳን እንዲሰደዱ አድርጓል፤ በርካታ ዜጎች እንዲታሰሩ እና የተለያየ ስያሜ በመሥጠት የሕዝቡን ንብረት እንዲወረስ አድርጓል ነው ያሉት።

​📉 ስልታዊ የሕዝብ አሰፋፈር ቅየራ በወልቃይት!

👉 30 ሺህ የቆሰሉ የሕወሃት ታጣቂዎች በጠገዴ ወረዳ ዲቪዥን በሚባል አካባቢ እስከ ቤተሰቦቻቸው አሥፍሯል ብለዋል።

👉 በ1977 ዓ.ም በድርቅ ምክንያት ወደ ሱዳን የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆችን በወልቃይት አሥፍሮ እንደነበርም አስታውሰዋል። የድርቅ መከላከል በሚል ፕሮግራም ከ15 ሺህ በላይ ሰዎችን በማስፈር የዲሞግራፊ ቅየራ ሥራ መተግበሩን ዶክተር ገሠሠው ተናግረዋል።

ሕዝቡ ማንነቱን እንዲያጣ፤ በቋንቋው እንዳይናገር እና ባሕሉን እንዳያራምድ በማድረግ በርካታ ወንጀሎችን መፈጸሙንም አስታውሰዋል።

በኢትዮጵያውያን ላይ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን በማስቀረት፤ የማንነት ጥያቄዎችን በማፈን፤ የዘር ፖለቲካን በመፍጠር፤ ጨቋኝ እና ተጨቋኝ የሚል የሃሰት ትርክትን በማራመድ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በርካታ ጫና ማሳደሩን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን በመካድ በ2013 ዓ.ም በመከላከያ ሠራዊት ላይ ክህደት በመፈጸም ለዓመታት ጦርነትን ማካሄዱንም አስታውሰዋል። በመጨረሻም ኢትዮጵያ ብታሸንፍም መንግሥት ለዘላቂ ሰላም ሲል የፕሪቶሪያን ስምምነት ፈርሟል ነው ያሉት። ሕገ ወጡ ሕወሃት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉም ጥሷል ብለዋል።

​⚠️ የፕሪቶሪያውን የሰላም🤝ስምምነትን ማፍረስ!

👉 ወታደራዊ ምልመላ አድርጓል፤ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ታጣቂ ኃይሎች ጋር ግንኙነት ፈጽሟል፤ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ተጋፍቷል ብለዋል። ሕገ ወጥ መፈንቅለ መንግሥትን ማካሄድ እና ሌሎች ተግባራትን በመፈጸም ስምምነቱን አፍርሷል ነው ያሉት።

ራያ ላይ ወረራ በመፈጸም ንጹሐንን በመግደል፤ ጠለምት ላይ ተፈናቃዮች ቢመለሱም ታጣቂዎች ካልተመለሱ በማለት በውይይት እንዳይፈታ እንቅፋት በመኾን፤ “አርሚ 70ን” ጨምሮ ሌሎች ታጣቂዎቹን በሱዳን ጦርነት በማሳተፍ በይፋ ስምምነቱን መጣሱን ተናግረዋል።

ሕወሃት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ሰላም እና መረጋጋት እንዳይመጣ ስጋት እና እንቅፋት የሚፈጥር የጥፋት ኃይል መኾኑንም አንስተዋል።

ጊዜያዊ አሥተዳደሩን በኃይል በመቆጣጠር፤ የሚዲያ ነጻነትን በመከልከል፤ እስከ ሞት ድረስ የሚያስቀጣ የወንጀል ሕግን በማውጣት የትግራይ ሕዝብን መከራ እያራዘመ መኾኑንም ተናግረዋል።

መንግሥት ለዘላቂ ሰላም ያለውን ፍላጎት በተደጋጋሚ በጠንካራ አቋሙ አሳይቷል ያሉት ዶክተር ገሠሠው በቀጣይ ሕግ ማስከበር ላይ ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማኅበር ምክትል ሥራ አሥኪያጅ ደረጀ ማሞ ሕወሃት ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያዊ ኾነው እንዳይኖሩ አድርጓል ብለዋል። የጦርነት አባዜ የግጭት ቀስቃሽነትን እና የፕሪቶሪያ ስምምነትን መጣሱን የዓለም ሕዝብ በማወቁ ዓለማቀፍ እገዳ እየተጣለበት መኾኑን ነው የጠቆሙት።

🔑 ተሰሚነት ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እና ኢትዮጵያውያን የጥፋት ኃይሉን ግጭት ቀስቃሽነት ለዓለም ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። የትግራይ ሕዝብ የጥፋት ኃይሉን ሴራ በመቃወም ራሱን መነጠል ይጠበቅበታል ብለዋል።

🔑 ኢትዮጵያውያን የሕገ ወጡ የሕወሃትን እንቅስቃሴ በመከታተል፤ በጥልቀት በመመርመር እና ሴራውን ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በማጋለጥ የኢትዮጵያን እውነታ ማሳወቅ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።

#አሚኮ_ዜና #የሕወሃት_ትንኮሳ #አማራ_ክልል_ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕርዳር_ሐምሌ_02/2018ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበአማራ ክልል በቀጣይ ቀናት የሚጠበቀውን የአየር ኹኔታ ምን ይመስላል?
Next articleሐምሌ አምስት ቀን ለሀገራዊ ለውጡ እርሾ የተጣለበት እና የሕወሃት ሽንፈት የተረጋገጠበት ቀን ነው።