
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 30ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ ቀርበው ከአባላቱ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ነው።
ባለፉት አምስት ዓመታት የብልጽግና ፓርቲን ወክለው የምክር ቤት አባል ኾነው ሲያገለግሉ የቆዩ እና በቀጣዩ አምስት ዓመታት የማይቀጥሉ አባላትን ስለነበራቸው አስተዋጽኦ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመስግነዋል።
በምክር ቤቱ ባይቀጥሉም በቀጣይ በመንግሥት አባልነታቸው ሀገር እና ሕዝብን እንዲያገለግሉም አስገንዝበዋል።
በተፎካካሪ ፓርቲ ተወክለው ባለፈው የምክር ቤት ዘመን በዕውቀታቸው፣ በአቅማቸው እና በመሻታቸው መጠን ሀገራቸውን ያገለገሉ እና በምክር ቤቱ ውስጥ ድምጻቸውን ያሰሙ አባላትንም አመስግነዋል።
በተካሄደው ምርጫ ምክንያት በምክር ቤቱ አባልነት የማይቀጥሉ አባላት ቢኖሩም ቀጣይ ከሚመሰረተው መንግሥት ጋር በመኾን ሀገር እና ሕዝብን ማገልገል እንደሚገባቸውም አንስተዋል።
የመንግሥት ምኞት የአባላቱ ተሳትፎ የመጨረሻ እንዳይኾን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት ውጭ እና ከመንግሥት ጋር በጋራ በመኾን ኢትዮጵያን እንዲያገለግሉም በምክር ቤቱ ላይ ጥሪ አቅርበዋል።
#አሚኮ_ዜና #የሕዝብ_ተወካዮች_ምክር_ቤት_ስብሰባ #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕርዳር_ሰኔ30_2018_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
በአሚናዳብ አራጋው
