
6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ሥብሠባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት በማካሄድ ላይ ይገኛል።
የምክር ቤቱ አባላት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙት ሀገራት ተርታ መሰለፏ የሁላችንም ኩራት ነው ብለዋል። መንግሥት እየተገበረ ባለው የኢኮኖሚ ሪፎርም በተጨባጭ አስተማማኝ ውጤት እየተመዘገበበት መኾኑንም ተናግረዋል።
በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ ትብብር የተወሰዱ እርምጃዎች እና የልማት ፖሊሲዎች በ2018 ዓ.ም የታቀደውን አጠቃላይ ዓመታዊ ጥቅል ምርት እድገት ለማሳካት ጠንካራ መሠረት መጣላቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የምትገኝበት የለውጥ ጉዞ ሀቅን ማየት እና እውነታን መቀበል የሚችል ሰው ይገነዘበዋል ነው ያሉት።
የዴሞክራሲ ባሕል እንዲጎለብት፤ መብቶች እና ነጻነቶች እንዲከበሩ እና የፖለቲካ ምኅዳሩ እንዲሰፋ የሚያስችል የፖለቲካ አውድ እንዲፈጠር፤ ለሀገር ሁለንተናዊ ብልጽግና መሠረት የሚኾን ሰፋፊ ሥራዎች እንዲሠሩ እና ሀገሪቱ በዓለም መድረክ ተቀባይነቷ እንዲጨምር የሚያስችሉ ሥራዎች በመከናወናቸው እውቅና ሰጥተዋል።
የምክር ቤት አባላቱ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከልም፦
👉 በ2018 ዓ.ም የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ከዋና ዋና መለኪያዎች አንጻር ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
👉 የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነት፣ የዋጋ ንረት እና መሰል ችግሮችን በአጭር እና በረጅም ጊዜ እቅድ ለመቅረፍ መንግሥት የጀመራቸው አዳዲስ መፍትሔዎች እና የወደፊት ስትራቴጅክ አቅጣጫዎች ምን ምን ናቸው?
👉 ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን በማንሳት ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ግጭት ውስጥ የሚገኙ ጽንፈኛ ኃይሎች እና ሌሎች ምን ትምህርት መውሰድ አለባቸው? መንግሥትስ ታላቁን ሕዝባዊ አደራ በተጨባጭ ለመተርጎም ምን ዝግጅት አለው?
👉 ብልሹ አሠራሮችን እና ሙስናን ለመቀነስ በዲጄታላይዜሽን ለመቅረፍ የተያዙ እቅዶች ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢሰጥባቸው? ሌብነት እና ሙስናን በመከላከል ልማቱ ወደማይደናቀፍበት ደረጃ እንዲደርስ የተያዙ እቅዶችስ ምን ምን ናቸው ? የሚሉ ጥያቄዎች ተሰንዝረዋል።
#አሚኮ_ዜና #የሕዝብ_ተወካዮች_ምክር_ቤት_ስብሰባ #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕርዳር_ሰኔ30_2018_ዓ_ም
በአድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
