ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር መንግሥት ምን እየሠራ ነው ?

6

 

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ሥብሠባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የምክር ቤቱ አባላምት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጥያቄዎችን እያነሱ ነው። ከተነሱት ውስጥ፦

👉 መንግሥት ከግብጽ፣ ከሱዳን እና ከኤርትራ ጋር በተያያዘ ያሉ ጠብ አጫሪነቶችን ለመከላከል እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር እና ለቀጣናው ሰላም መረጋጋት ምን ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ ስትራቴጅ እየተከተለ ነው?

👉 አሁንም በክልሎች ግጭት፣ ብሔር ተኮር ጥቃት አለ፤ መፍትሔው ምን ይሁን?

👉 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ተገቢውን ውጤት ማምጣት አልቻሉም? በርካታ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ እያመጡ አይደለም? በርካታ ተማሪዎች ትምህርት ላይ አይደሉም መፍትሔው ምንድን ነው ?

👉 ለወጣቶች በበቂ ሁኔታ የሥራ ዕድል እየተፈጠረ አይደለም።

👉 ለሰብዓዊ መብት መከበር መንግሥት ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። በጦርነት፣ በግጭት ምክንያት በርካታ ዜጎች ለሰብዓዊ እርዳታ ተጋልጠዋል። ድጋፍ እየተደረገላቸው አይደለም።

👉 ለሀገር ሰላም እና ልማት እውነተኛ ብሔራዊ ውይይት ማድረግ እና በፖለቲካዊ መፍትሔ መፍታት ይገባል?

👉 ሀገራዊ ምክክሩን ከመንግሥት የፖለቲካ ተጽዕኖ ነጻ ማድረግ ያስፈልጋል?

👉 በክልሎች የሃብት ክፍፍልን ፍትሐዊ ለማድረግ ምን ታስቧል?

👉 ሀገር አቋራጭ የባቡር መሥመር ግንባታ እና ለመስኖ ልማት የሚውሉ ግድቦች መዘርጋት ምን ታቅዷል?

👉 አምራች ዘርፎችን ለማጠናከር እና በሕዝብ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ላይ የሚታይ ለውጥ ለማምጣት ምን ታቅዷል?

👉 በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል መንግሥት ምን ዓይነት የክትትል ሥርዓትን እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ምን እየተሠራ ነው?

#አሚኮ_ዜና#የሕዝብ_ተወካዮች_ምክር_ቤት_ስብሰባ#አማራ_ክልል_ኢትዮጵያ🇪🇹#ባሕርዳር_ሰኔ30_2018_ዓ_ም

በያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 30ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
Next article