የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 30ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

5

 

በዕለቱ በምክር ቤት አባላት ከተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች መካከል:-

👉 ሀገራዊ ምክክሩ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ መንግሥት ምን አይነት የሎጀስቲክስ፣ የፖለቲካ እና ተቋማዊ ድጋፍ እያደረገ ነው?

👉 ምክክሩ ያለመሰናክል እንዲሳካስ ከእያንዳንዱ ዜጋ ምን አይነት ኀላፊነት ይጠበቃል?

👉 ተጀምረው የተጓተቱ እና ያልተጠናቀቁ ትላልቅ ፕሮጀክቶች እና ታቅደው ላልተጀመሩ ፕሮጀክቶች ምን የታሰበ ነገር አለ?

👉 በልማት ፕሮጀክቶች ተነሺ ለኾኑ የማኅበረሠብ ክፍሎች ተገቢውን ማቋቋሚያ እንዲሠጣቸው በማድረግ በኩል ምን የተቀመጠ አቅጣጫ አለ?

👉 በኑሮ ውድነት፣ በቤት ችግር እና በገቢ ማነስ ለተቸገሩ የመንግሥት ሠራተኞች እና ለዝቅተኛ ነዋሪ የኅብረተሰብ ክፍሎች ኑሮውን ለማሻሻል ምን የታሰበ ነገር አለ? አዲስ ከሚመሠረተው መንግሥት ምን ይጠበቃል?

👉 በአዲስ አበባ የተጀመረው የተማሪ ምገባ መርሐ ግብር ወደ ሌሎች ክልሎች እንዲሰፋ ለክልሎች አስገዳጅ ኾኖ ቢቀርብ?

👉 የኦዲት ጉድለት የሚገኝባቸው ተቋማት አሥፈጻሚዎች ለምን ተጠያቂ አይኾኑም? መንግሥት እንዴት ሊያስተካክለው አስቧል?

👉 የወደብ ጉዳይ የሉዓላዊነት ጉዳይ ነው ተብሎ ሢሠራ ቆይቷል፤ በመንግሥት በኩል አሁን ላይ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ማብራሪያ ቢሰጥ?
የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል።

#የሕዝብ_ተወካዮች_ምክር_ቤት #ኢትዮጵያ #ሀገራዊ_ምክክር #ዘላቂ_ሰላም #የኑሮ_ውድነት #ልማት_ፕሮጀክቶች #የኦዲት_ተጠያቂነት #የወደብ_ጉዳይ #AMECO #አሚኮ
#ባሕርዳር_ሰኔ_30_2018ዓ_ም

በአሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleከታሪክ የማይማረው የሕወሓት የጥፋት ጉዞ
Next articleብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር መንግሥት ምን እየሠራ ነው ?