
ሦስተኛው ሀገራዊ “የጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ ንቅናቄ” ዛሬ ተጀምሯል።
በዚህ የማስጀመሪያ መድረክ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ፣ የክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
📊 በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር) መንግሥት የአካባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎችን በጽናት በመቋቋም ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ ፖሊሲዎችን እና ፕሮግራሞችን በቁርጠኝነት እየተገበረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
📌ለዚህም ማሳያ ከሚኾኑ ዋና ዋና ክንዋኔዎች መካከልም፦
✍️የ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ እና የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር፤
✍️የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ እና የንጹሕ አየር ጥምረት፤
✍️የከተማ ኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች፤
✍️አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የላስቲክ ከረጢቶችን የሚከለክል ሕግ፤
✍️ የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር የማስገባት ክልከላዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል።
የአየር ንብረት ለውጥን በዘላቂነት ለመከላከል እንደ ሀገር እየተሠራ ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከፍተኛ ውጤት ማስገኘቱንም ጠቁመዋል። አሁን እየተተገበረ የሚገኘው የጽዱ ኢትዮጵያ” ሀገራዊ ንቅናቄ ንጹሕ እና ጤናማ አካባቢን ለመፍጠር ትልቅ አቅም መኾኑን አስገንዝበዋል።
ይህ ንቅናቄ በተለይም በከተሞች እና በገጠር አካባቢዎች የጽዳት ባሕል እንዲጠናከር፤ በቆሻሻ አያያዝ ላይ የሕዝብ ግንዛቤ እንዲጨምር እና የአካባቢ ጥበቃ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኀላፊነት መኾኑን አውቆ የባለቤትነት ስሜት እንዲፈጥር ማስቻሉን አብራርተዋል።
📢 ንቅናቄው ይበልጥ ስኬታማ እንዲኾን ትምህርት ቤቶች፣ ተቋማት፣ ፋብሪካዎች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በልዩ ትኩረት እና በትጋት እንዲሠሩ ሚኒስትሯ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
#ፅዱኢትዮጵያ #አረንጓዴአሻራ #የአየርንብረትለውጥ #ዘላቂልማት #ኢትዮጵያ
ዘጋቢ: ኢብራሂም መሐመድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
