ለጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ስኬታማነት በትኩረት መሥራት ይገባል።

13

 

ሦስተኛው ሀገር አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄ “ጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ” ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ (ዶ.ር) በመደመር ዕሳቤ ተግባራዊ በኾኑት የአረንጓዴ አሻራ፤ የወንዝ ዳርቻ ልማት፤ የከተማ እና የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራዎች ለአካባቢ ጥበቃ እና ልማት ትልቅ ውጤት ተገኝቶባቸዋል ብለዋል።

👥 ባለፉት ሁለት ዙሮች የብክለት ቅነሳ ንቅናቄዎች ላይ በገፅ ለገፅ 23 ሚሊዮን ሕዝብ፤ በመገናኛ ብዙሃን በተሠሩ ሥራዎች 70 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን ግንዛቤ ማሳደግ ተችሏል ነው ያሉት።

⚖️ የአካባቢ ጥበቃ ሕጎች ተሻሽለው በመውጣታቸው በአካባቢ ጥበቃ ሥራ ላይ የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል።

🎯 የዘንድሮው ትኩረት፦

ዛሬ የተጀመረው እና ለተከታታይ ሦስት ወራት የሚካሔደው የብክለት ቅነሳ ንቅናቄ በዋናነት በፕላስቲክ ብክለት፤ በአደገኛ ቆሻሻ ብክለት እና በድምፅ ብክለት ላይ ትኩረት ያደርጋል ነው ያሉት።

ጽዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ በማሻገር ሂደት ላይ እያንዳንዱ ዜጋ የበኩሉን ኀላፊነት እንዲወጣ ለሊሴ ጥሪ አቅርበዋል።

🇪🇹 ለአረንጓዴ እና ጽዱ አካባቢ ሁላችንም አሻራችንን እናኑር !

#ፅዱኢትዮጵያ #ለቅን_ትውልድ #የአካባቢጥበቃ #የኮሪደርልማት #አረንጓዴአሻራ #Ethiopia
#አዲስ_አበባ: #ሰኔ 27/2018ዓ.ም

ዘጋቢ፦ ኢብራሒም መሃመድ

Previous article” መንግሥት ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ ፖሊሲዎችን እና ፕሮግራሞችን በቁርጠኝነት እየተገበረ ነው” ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር
Next articleዕውቀታችሁን ለሀገር ግንባታ አውሉ።