
ባሕር ዳር: ሰኔ 24/2018 ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ “ለሀገር ግንባታና ለዘላቂ ሰላም የማኅበረሰቡ ሚና” በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።
የደቡብ እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጄር ጄኔራል ደስታ ተመስገን በጽንፈኝነት አስተሳሰብ እና በትጥቅ ትግል ሰላማዊ የሕዝብ እንቅስቃሴን ማረጋገጥ አይቻልም ብለዋል። ሠራዊቱ ከክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የጽንፈኛ ኀይሎችን ያልተገባ እንቅስቃሴ ለማድረቅ እያደረገ ያለዉን ጠንካራ ስምሪት መደገፍ እንደሚገባ አንስተዋል።
እናቶች ጥቁር እንዲለብሱና አባቶች እንዲያዝኑ አንሻም ብለዋል። ጽንፈኛው ኀይል በተሳሳተ ትርክት ወጣቱን መልምሎ በማሠልጠን እና ለጥፋት በማሰማራት የባዕዳን ጠላቶችን ተልዕኮ ማስፈጸሚያ ማድረጉን ተናግረዋል።
ጸረ ሰላም የሕዝብን ንብረት እንደሚዘርፍም አንስተዋል። ሠራዊቱ እየወሰደ ባለው የተጠናከረ እርምጃ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ገልጸዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር ሠራዊቱ ለሕዝብ የቆመ የሰላም አምባሳደር ነው ብለዋል። ኅብረተሰቡ ያለ ምንም የጸጥታ ስጋት ወጥቶ እንዲገባ በጠላት ተፅዕኖ ወደ ጫካ የገቡ ወጣቶች ትጥቃቸውን ፈትተዉ ወደ ኅብረተሰቡ እንዲመለሱ እና ሰላማዊ ሕይወታቸዉን እንዲመሩ በትኩረት እተየሠራ መኾኑን አስገንዝበዋል።
ከሀገር መከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች
ከሠራዊቱ ጎን በመቆም ለአካባቢው ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ተናግረዋል።
#አሚኮ_ዜና #የሀገር_መከላከያ_ሠራዊት_ሕዝባዊ_ውይይት #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!።
