📝 የኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማከናወን ይገባል።

4

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 24/2018 ዓ.ም የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ጥራት ያለው መረጃን ለመሠብሠብ እና ለመመዝገብ እየሠራ ይገኛል።

ይህ ተግባር ለሀገር አቀፍ ስታቲስቲክስ ዝግጅት እና ለመንግሥት አሥተዳደር ወሳኝ ሚና አለው።

​የአማራ ክልል ሲቪል እና ቤተሠብ ምዝገባ አገልግሎት ኀላፊ መዓዛ በዛብህ ቴክኖሎጂው የጠራ መረጃን ለማደራጀት እና ቅብብሎሽን ቀላል እና ፈጣን ለማድረግ ማስቻሉን ገልጸዋል።

በተለይም መረጃው ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲውል ለማስቻል ታልሞ ጥረት እየተደረገ መኾኑንም አንስተዋል።

ምዝገባውን ተደራሽ ለማድረግ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች እየተሠራ ነው ብለዋል። ኩነቶችን በወቅቱ ምዝገባ ለማከናወን ጥረት መደረጉንም አንስተዋል።
የልደት፣ የሞት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እና የጉዲፈቻ ምዝገባ እንደሚከዎን ነው የተናገሩት ።

የልደት 90 ቀናት፣ ሞት 50 ቀናት እና ሌሎች ኩነቶች ደግሞ በ30 ቀናት ውስጥ የሚካሄደው ምዝገባ ሙሉ በሙሉ ከክፍያ ነጻ ነው ብለዋል። ከተቀመጠው ጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ የሚጠየቀው ከፍተኛ ክፍያ 300 ብር ብቻ ነው ያሉት ኀላፊዋ ከዚህ በላይ ክፍያ የሚጠይቅ አካል ካለ አግባብ ባለው አካል በኩል ማሳወቅ ይገባል ነው ያሉት።

በተለይም በጸጥታ ችግሮች ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ ሀሰተኛ ሰነዶችን ለመከላከል ኅብረተሰቡ በንቃት እንዲከታተል እና ለሚመለከተው አካል እንዲያሳውቅ አስገንዝበዋል።

​በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባርም ሕጻናት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ከመሄዳቸው በፊት የልደት ምስክር ወረቀታቸውን አስቀድመው እንዲያወጡ ወላጆች ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

#የኩነቶች_ምዝገባ #የልደት_ምስክር_ወረቀት #ከክፍያ_ነፃ #CivilRegistration #CRVS #FreeRegistration #AmharaRegion

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

Previous articleበክረምት ሊከሰቱ የሚችሉ የጎርፍ አደጋዎችን ለመከላከል እየተሠራ ነው።