በአማራ ክልል 100 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ይወስዳ

4

 

#ባሕር_ዳር: ሰኔ 23/2018 ዓ.ም
በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ተጀምሯል። የፈተናውን አጀማመር የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሥራ ኀላፊዎች በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተገኝተው ምልከታ አድርገዋል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ጥላሁን ወርቅነህ በክልሉ 99 ሺህ 848 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ተናግረዋል።

ለተማሪዎች የማካካሻ እና የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ሰፊ ድጋፍ ተደርጓልም ነው ያሉት። ተማሪዎች በበይነ መረብ ተፈታኝ በመኾናቸው ቀድመው እንዲለማመዱ ተደርጓል ብለዋል።

ፈተናው በ6 ዙር ይሰጣልም ነው ያሉት ኀላፊው በ23 ማዕከላት ላይ ዛሬ ፈተና እየተሰጠ እንደኾነም ጠቁመዋል።
2 ሺህ 135 ኮምፒዩተሮች ተገዝተው ተማሪዎች በምቹ ሁኔታ እንዲፈተኑ ማድረግ ተችሏልም ነው ያሉት።

አጀማመሩን በማየት ክፍተቶች ካሉ ለማስተካከል እና ድጋፍ ለማድረግ ምልከታ መደረጉንም ተናግረዋል። ባለድርሻ አካላት ከትምህርት ቢሮ ጋር በመኾን የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋልም ነው ያሉት።

ትምህርት ሰላም ይፈልጋል ያሉት ኀላፊው ሁሉም ማኅበረሰብ ለተማሪዎች እንክብካቤ በማድረግ፣ ሰላምን በማጽናት፣ ፈታኝ እንግዶችን በመንከባከብ ለፈተናው ስኬት እና ለተማሪዎች ውጤታማነት ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

#አሚኮ_ዜና #NationalExamEthiopia 🇪🇹

ዘጋቢ:-ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!።

Previous articleበሀረሪ ክልል ሁሉም ኩነት በዲጂታል አሠራር እየተከናወነ ነው።