በሀረሪ ክልል ሁሉም ኩነት በዲጂታል አሠራር እየተከናወነ ነው።

5

 

ባሕር_ዳር: ሰኔ 23/2018 ዓ.ም ሁሉንም የኩነት ምዝገባዎች ሙሉ በሙሉ በዲጂታል አሠራር እያከናወነ እንደሚገኝ የሀረሪ ክልል ወሳኝ ኩነት እና ምዝገባ ኤጀንሲ ኀላፊ ሳዳም መሐመድ ገልጸዋል።

ኤጀንሲው በሁሉም ወረዳዎች እና የጤና ተቋማት የዲጂታል የኩነት ምዝገባዎችን ተግባራዊ ማድረግ ተችሏል።

በ2018 በጀት ዓመትም በአጠቃላይ ከ15 ሺህ በላይ ኩነቶች በዲጂታል ምዝገባ ማከናወን መቻሉን ጠቁመዋል።

ኤጀንሲው ከወረዳዎች በተጨማሪ በጤና ተቋማት የልደት እና ሞት ምዝገባን በአንድ ማዕከል እያከናወነ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ምዝገባው ሙሉ በሙሉ በዲጂታል የተደገፈ መኾኑ የተጣራ የጤና እና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት ያስችላል ብለዋል፡፡

ኤጀንሲው ከ 2015 ዓ.ም በፊት የተመዘገቡ የነዋሪዎችን መረጃ በዘመናዊ መንገድ ለማደራጀት ወደ ዲጂታል የመቀየር ሥራ እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን እውን ለማድረግ ፖሊሲ ተቀርፆ ወደ ሥራ መገባቱን የገለጹት ኀላፊው ኤጀንሲው እያከናወነ የሚገኘውን መረጃ ወደ ዘመናዊ ሥርዓት የማስገባት ተግባር ለሌሎች ሥራዎችም መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል።

በተለይ የነዋሪዎችን መረጃ በዲጂታላይዜሽን መንገድ በማደራጀት ሌብነትን እና ብልሹ አሠራርን ለመቅረፍ ሁነኛ ሚና አለው ነው ያሉት።

የወሳኝ ኩነት ምዝገባዎች ለሕጋዊ፣ ለአሥተዳደራዊ እና ለስታትስቲክስ ዓላማዎች ጥቅም ላይ እንደሚውሉም አስገንዝበዋል ።

በተለይ በአንድ ሀገር በዜጎች ከልደት እስከ ህልፈተ-ሕይወት የሚከሰቱ ወሳኝ ኩነቶች እንደ ልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ እና ሞት ያሉ ክስተቶች የአንድን ሀገር ቀጣይ የልማት አቅጣጫ የመወሰን አቅም ያላቸው መኾኑን ጠቁመዋል።

ኤጀንሲው ቅንጅታዊ አሠራሩን በማጎልበት በጤና ተቋማት የኩነት ምዝገባ አገልግሎትን ለማስፋት እየሠራ በመኾኑ ዜጎችም እያንዳንዱን ኩነት በወቅቱ በማስመዝገብ የዜግነት ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

#አሚኮ_ዜና #CRVS (Civil Registration and Vital Statistics)🇪🇹

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!።

Previous articleየክልሉን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ትልቅ የሚሊሻ ኀይል ተገንብቷል።
Next articleበአማራ ክልል 100 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ይወስዳ