
ደሴ: ሰኔ 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ፓረኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የተቀናጀ ሥራ አመራር ሥርዓቶችን በመዘርጋት፣ ጥራት ላይ ትኩረት በመስጠቱ በዓለም አቀፍ የጥራት መስፈርቶች በብቃት በማለፍ የዓለም አቀፍ ሰርትፍኬት(አይኤስኦ) ማግኘቱ ተመላክቷል።
የኮሞቦልቻ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ከአካባቢ ጋር ተስማሚነት ያላቸው ተግባራትን ማከናወኑ ለዕውቅና እንዳበቃው የኮምቦልቻ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽዳት እና ውበት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ደሳለኝ እጅጉ ተናግረዋል። ሌሎቹም ተቋማት የኢኮኖሚክ ዞኑን ተሞክሮ መውሰድ እና መተግበር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የኮሞቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዓለም አቀፍ ሰርትፍኬት ያገኘው በጥራት ሥራ አመራር፤ በአካባቢ ጥበቃ፣ በሥራ ላይ የጤና እና ደኅንነት በፈፀማቸው ቁልፍ ተግባራት መኾኑን በኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮር ፖሬሽን የኮምቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዋና ሥራ አሥኪያጅ አህመድ ሰይድ ተናግረዋል።
የኢኮኖሚ ዞኑ ሲቋቋም የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የዕውቀት ሽግግር ማድረግ የተቋቋመባቸው ዋና ዋና ዓላማዎች ናቸው ብለዋል።
በቀጣይም በሁሉም መመዘኛ መስፈርቶች ጠንክሮ በመሥራት ከውጭ ምንዛሬ የሚገኝ ገቢን ለማሳደግ እንደሚሠራ ተናግረዋል።
ዓለምአቀፍ መስፈርቶችን በብቃት በማለፍ የተገኙ ሰርትፍኬቶች የተሻለ አቅም ያላቸው እና ዓለምአቀፍ ባለሃብቶችን ለመሳብ ሚናቸው የላቀ መኾኑን አስረድተዋል።
በኢትዮጲየያ የተስማሚነት ኤጀንሲ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሚሻሞ ዋካሶ የኮምቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ያገኛቸው ሰርትፍኬቶች የሚያመርታቸውን ምርቶች ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ተመራጭ እንደሚያደርጉትም ተናግረዋል።
የተገኙ ወጤቶች ብዙ የተደከመባቸው መኾናቸውን አመላክተዋል።
የኮሞቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዓለምአቀፍ ሰርትፍኬቶችን አንዲያገኝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሠራተኞች ማበረታቻ እና ዕውቅና ተሰጥቷል።
#አሚኮ_ዜና #ኮምቦልቻ_ኢንዱስትሪ_ፓርክ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
ዘጋቢ፦ደምስ አረጋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
