🇪🇹 ኢትዮጵያ በምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር የአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመኾን እየሠራች ነው 💊

3

 

ኢትዮጵያ ከውጪ የምታስገባው የምግብ እና የመድኃኒትን ፈዋሽነት ለመገምገም የሚያሥችል ዓለም ዓቀፋዊ እና አሕጉራዊ ስምምነቶችን ፈርማ እየሠራች ትገኛለች።

የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር መለኪያ ላበራቶሪ እድሳት ተደርጎለት ወደ ሥራ መግባቱን ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን በዓለም ዓቀፉ የመድኃኒት መለኪያ በ2025 በተደረገው የመድኃኒት መለኪያ ቁጥጥር ከኢጋድ ሀገራት የመጀመሪያውን ደረጃ መያዟን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ተናግረዋል።

ተቋሙ ዓለም ዓቀፍ እውቅና ያገኘው በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አሥተዳደሮች በምግብ መድኃኒት ቁጥጥር ባስመዘገብነው ውጤት የተገኘ ነውም ብለዋል።

ምርትን መሠረት ያደረገ ቁጥጥር ከክልል ወደ ክልል የሚሸጋገሩ የተቀነባበሩ ምግቦችን፣ መድኃኒቶች፣ የሕክምና መሳሪያዎች፣ የውበት መጠበቂያዎች እና የትንባኾ ምርቶች ላይ ቁጥጥር ማድረግ የተቋሙ ኀላፊነት መኾኑንም ገልጸዋል።

ግልጽ፣ ቀልጣፋ እና ፈጣን ሥራዎችን ለመሥራት ጥረት እየተደረገ ነው የሚሉት ዳይሬክተሯ እንደ ሀገር በተሠራው የሪፎርም ተግባር እስካሁን ለተገኘው ውጤት እና ዓለም ዓቀፍ ስታንዳርድ ለመጠበቅ አግዞናል ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ እየተሠራ ያለው የምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ማደግ ጤናማ ኅብረተሰብ ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል።

#FoodAndDrugRegulation #CenterOfExcellence #PublicHealth #IGAD #Ethiopia #HealthcareQuality

ዘጋቢ፦ አየለ መስፍን

Previous articleየቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ብልጽግና ፓርቲ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማሸነፉን ተከትሎ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፈ።