በዋትስአፕ ተጠቃሚዎች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት፦

3

 

ባሕር ዳር:ሰኔ 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዋትስአፕ ተጠቃሚዎች ላይ ያነጣጠረ እና የኮምፒውተሮችን ደህንነት ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥል አዲስ የማጭበርበር (Phishing) እየተሰራጨ ነው።

ጥቃቱ በብዙ ሀገራት ላይ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ካስፐርስኪ (Kaspersky) የተሰኘ የመረጃ ምንጭን ዋቢ አድርጎ ኢንሳ አስነብቧል።

ጥቃት በተለይ በሥራ ቦታቸው ሰነዶችን ለመለዋወጥ ዋትስአፕን በኮምፒውተራቸው ላይ በሚጠቀሙ (WhatsApp Web/Desktop) የመንግሥት እና የግል ተቋማት ሠራተኞች እንዲኹም ነጋዴዎች ላይ ስጋት ኾኗል ተብሏል።

👉ጥቃቱ እንዴት ይፈጸማል?

#የታመኑ አካውንቶችን መጠቀም፦ ጠላፊዎች ቀደም ሲል የጠለፏቸውን የዋትስአፕ አካውንቶች በመጠቀም፣ በላኪው የስልክ ማውጫ (Contact List) ውስጥ ላሉ የንግድ አጋሮች እና ጓደኞች አደገኛ ፋይሎችን ይልካሉ።

#አሳሳች ስያሜዎች፦ ፋይሎቹ የተጠቃሚዎችን ትኩረት ለመሳብ ሲባል እንደ “የሂሳብ ሪፖርት” (Financial Report)፣ “የክፍያ ማሳሰቢያ” (Billing Statement) ወይም “የባንክ ማስታወቂያ” የሚሉ የሐሰት ስያሜዎች ይኖራቸዋል።

#ኮምፒውተርን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር፦ ተጠቃሚው ፋይሉን (VBScript file) አውርዶ ሲከፍተው፣ ቫይረሱ ከጀርባ የኮምፒውተሩን የደህንነት ሲስተም በመስበር የራሱን ሶፍትዌር ይጭናል።

ይህም ጠላፊዎቹ የተጠቂውን ኮምፒውተር ከርቀት (Remote Access) ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠሩትና ምስጢራዊ መረጃዎችን እንዲሰርቁ ያስችላቸዋል።

👉ጥንቃቄውስ?

#ሳያረጋግጡ ፋይል አለመክፈት፦ ከሚታወቅ የንግድ አጋር ወይም የሥራ ባልደረባ ቢላክም፣ አስቀድመው ያልጠበቁት ወይም ያላዘዙት የፋይል መልዕክት ሲደርስ ከመክፈት በፊት ለላኪው በስልክ በመደወል ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ ተገቢ ነው።

#የጸረ-ቫይረስ (Antivirus) ሶፍትዌር መጠቀም፦ ማንኛውንም ከበይነ መረብ ወይም ከዋትስአፕ የወረደን ፋይል ከመክፈት በፊት ሁልጊዜ በዘመነ የጸረ-ቫይረስ ሶፍትዌር መፈተሽ

•#አጠራጣሪ ፋይሎችን መለየት በዋትስአፕ በኩል የሚላኩ እና መጨረሻቸው .vbs የኾኑ ፋይሎችን በፍጹም በኮምፒውተር ላይ አለመክፈት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሚሊሻ የሕዝብ ዘብ ነው።
Next article“ሠራዊቱ በጸረ ሽምቅ ስምሪት ያስመዘገባቸው ድሎች የተላላኪዎችን አንገት ያስደፋ እና ሰላም ወዳዱን ሕዝብ ያስደሰተ ነው” ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማ