
ጎንደር፡ ሰኔ 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ “በሚል መሪ መልዕክት የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው የበጎፍቃድ አገልግሎት ሕዝብ እና መንግሥት ተቀራርቦ ችግሮችን የሚፈታበት የሀገር ፍቅር መገለጫ መኾኑን ተናግረዋል።
በክረምት መርሐ ግብሩ ከ270ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለማሳተፍ መታቀዱም ተገልጿል። ከ4 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ የደን እና ፍራፍሬ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉም ተመላክቷል።
በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሐ ግብሩ ድጋፍ የሚሹ አካላትን መደገፍ፣ የአረንጎዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ የትምህርት፣ የሥልጠና አገልግሎት እና የጤና አገልግሎት በዋነኝነት ትኩረት የሚሰጣቸው ሥራዎች መኾናቸውም ተገልጿል።
ባለፈው ዓመት “ሥራን በማላቅ ወደ ባሕል ማሻገር” በሚል መሪ መልዕክት የተካሄደው የክረምት በጎፍቃድ አገልግሎት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡም ተጠቅሷል።
#አሚኮ_ዜና #የበጎ_አድራጎት_ሥራ #ጎንደር #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
ዘጋቢ፦ አፈወርቅ ደሴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
