ከወሰዳቸው የትምህርት መስኮች 43ቱን A+ እና ዘጠኙን A በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ የኾነው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ።

17

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 492 ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች እና ደረጃዎች እያስመረቀ ነው። በምርቃቱ ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ ተመራቂዎች የዋንጫ እና የሜዳሊያ ተሸላሚ ኾነዋል።

ከተመራቂዎች መካከል በቢዝነስ ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የትምህርት መስክ የተመረቀው ተማሪ እዝራ አንዱዓለም በዩኒቨርሲቲው ከወሰዳቸው አጠቃላይ የትምህርት መስኮች መካከል 43ቱን A+ እና ዘጠኙን A በማምጣት ሙሉ 4 ነጥብ ማስመዝገብ ችሏል።

ባለ ብሩህ አዕምሮው ተመራቂ እዝራ ዋንጫውን ከክብር እንግዳው እጅ ተቀብሏል። ተመራቂው ባደረገው ንግግር ለተመራቂዎች እና ቤተሰቦቻቸው በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል።

ዛሬ ላይ የሚያስደስት እና የተመቻቸ ሕይወት ላይኖር ይችላል፣ ነገር ግን በብርታት እና በተስፋ መቀጠል ይኖርብናል ነው ያለው።

ለዚህ ምርቃት ስንበቃ በኹሉም ነገር በቅተን አለመኾናችንን መገንዘብ ያስፈልገናል፤ ይልቁንስ ወደፊት ትምህርታችንን ቀጥለን ብቁ ተማሪዎች መኾናችንን መቀጠል እንዳለብን መዘንጋት አይገባንም ብሏል።

በቀጣይም ትምህርታችንን ቀጥለን ማንኛውም እናት እና ሀገር የምትኮራበት እንድንኾን ተግተን መሥራት ይገባናል ነው ያለው።

ስኬታማ እንዲኾን ያገዙትን ሁሉ አምስግኗል።

#አሚኮ_ዜና #የባሕር_ዳር_ዩኒቨርሲቲ_የተማሪዎች_ምረቃ #ባሕር_ዳር #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ ፦ አድኖ ማርቆስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ተመራቂዎች በሙያችሁ የሀገር አለኝታ መኾን ይገባችኋል” ፕሮፌሰር በላይ ካሳ
Next articleተመራቂ ተማሪዎች ከዘመናዊው ዓለም ጋር ራሳቸውን ማዋሐድ አለባቸው።