
ባሕር ዳር: ሰኔ 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን 6 ሺህ 492 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው የምርምር ተቋም እንደመኾኑ በሦስተኛ ዲግሪ አስተምሮ በዶክትሬት ዲግሪ በማስመረቅ በኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል ብለዋል።
በአካዳሚክ ምርምር እና አዳዲስ እውቀቶችን በማፍለቅ ከፍተኛውን የትምህርት ደረጃ ማረጋገጫ በማግኘት 152 ተማሪዎች በዶክትሬት ዲግሪ አስመርቋል ነው ያሉት።
ይህ ቁጥርም በዩኒቨርሲቲው ታሪክ የመጀመሪያ መኾኑን ገልጸዋል።
#አሚኮ-ዜና #ባሕርዳር-ዩኒቨርሲቲ #ምርቃት2018
