የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የውይይት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

6

 

የክልሎችና የከተማ አሥተዳደሮች የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በግምገማ መድረኩ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የሶማሊ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ ፣ በብልፅግና ፓርቲ የፓለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ.ር) ፣በብልፅግና ፓርቲ የሶማሊ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አብድራሀማን አህመድ የሁሉም ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የፓለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ.ር ) ብልፅግና ፓርቲ አግላይ እና የበላይ እሳቤን በማስወገድ በእኩልነት የተመሰረተ አካታች የፖለቲካና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን እውን በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ በማምጣት በስኬት እየተራመደ ይገኛል ብለዋል።

የፓርቲውን እሳቤ ወደ ማኅበረሰቡ በማስረጽ አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት የማድረግ አላማ ያለውን መድረክ ላዘጋጁ የክልሉ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል።

ለዘመናት ከመሀል ፖለቲካ ተገልሎና ከሀገሪቱ ኢኮኖሚ ፍትሀዊ ተጠቃሚ ሳይሆን የኖቆየው የሶማሊ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት በመሐል ፖለቲካና ኢኮኖሚ ላይ ያለው ተሳትፎ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለማሳደግ መቻሉን ተናግዋል።

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የሶማሊ ክልል ሕዝብ ለዘመናት ሲናፍቅ የቆየውን እንደ ጤና፣ መንገድና ትምህርት የመሳሰሉ የመሰረተ ልማት አውታሮች በስፋትና በጥራት ተጠቃሚ ለመሆን መብቃቱን ኀላፊው ጨምረው ገልፀዋል ።

በመድረኩ ላይ የክልሎችና የሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 በጀት አመት እቅድ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

Previous articleወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።