
ባሕር ዳር: ሰኔ 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ አፍሪካ የፀረ-ስደተኞች እንቅስቃሴ መሪዎች በሀገሪቱ የሚገኙ ስደተኞች እስከ 23/10/2018 ዓ.ም ድረስ ሀገሪቱን እንዲለቁ ማሳሰባቸውን ቢቢሲ አስታውሷል።
‘ማርች ኤንድ ማርች’ የተሰኘው ይህ እንቅስቃሴ በመሪው አማካኝነት የተቀመጠው ቀነ ገደብ ለውጥ እንዳለተደረገበት መግለጹን ተከትሎ ስጋቶች ጨምረዋል።
በዚህ አመጽ ኢትጵያውያንም ስጋት ውስጥ ናቸው። በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ጋር በቅርበት እየሰራ መኾኑን ገላጿል።
በዚህም የሀገሪቱ መንግሥት በቀጣይ ቀናት የፀጥታ ማስከበር ተግባሩን እንደሚያጠናክር ይጠበቃል” ብሏል ኢምባሲው።
ነገር ግን በስደተኞች ላይ ሕገ ወጥ ድርጊት እና ጥቃቶች ሊፈጸሙ የሚችሉበት ኹኔታዎች እንዳሉ የሚጠቁሙ አዝማሚያዎች እንደሚስተዋሉ ጠቁሟል።
በመኾኑም ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንቅስቃሴቸው በጥንቃቄ እንዲኾን አሳስቧል።
ከመንግሥት አካላት እና ከማኅበረሰብ አደረጃጀቶች ጋር የቅርብ ግንኙነት ማድረግ፤ መረጃ መለዋወጥ እና አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማከናወን እንዳይረሳም ኢምባሲው አሳስቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
