
ባሕር ዳር: ሰኔ 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በጓንጓ ወረዳ ጥሩ ብርሃን ቀበሌ ድባራ ጎጥ አምላና ተፋሰስ 🌳 የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተክለዋል።
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) አርሶ አደሮችን በማደራጀት በ54 ሄክታር መሬት 🥑የአቮካዶ ችግኝ መተከሉን ተናግረዋል። በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርም ለክላስተር ልማት ትኩረት ተሰጥቷል ነው ያሉት።
ከደን ችግኝ ተከላ ጎን ለጎን በ2018 በጀት ዓመት 🍒ለአትክልት እና ፍራፍሬ ችግኝ ልማት ትኩረት እንደተሰጠም ገልጸዋል።
በክልሉ የፍራፍሬ ልማት ውጤት በአርሶ አደሮች ላይ የአመለካከት ለውጥ አምጥቷልም ብለዋል። በምሥራቅ አማራ🍌የሙዝ እና 🥭የማንጎ ክላስተር እንዲሁም በምዕራብ አማራ 🥑አቦካዶ እና ቡና ትኩረት ተሰጥቷቸዋል ነው ያሉት።
ማኅበረሰቡ የትክልት እና ፍራፍሬ ልማትን ጥቅም ተረድቷል ያሉት ዶክተር ድረስ የፍራፍሬ ልማት የክልሉን ገቢያ እየሸፈነ ነው ብለዋል።
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) 🌳በአረንጓዴ አሻራ የአትክልት እና ፍራፍሬ ክላስተር ልማት ለገበያ እና ለፍብሪካ አቅርቦት እንዲኾን ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል። በክልሉ የደን ሽፋን ዕድገት ማሳየቱንም ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ደረጀ ማንደፍሮ በክልሉ 🥑የአቮካዶ ልማት አርሶ አደሮችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እያደረገ እንደኾነ ነው የጠቆሙት።
የክልሉን ጸጋ በአግባቡ በመጠቀም የክላስተር ልማትን ለማስፋት ተሠርቷልም ብለዋል። አረንጓዴ አሻራ ለወጣቶች የሥራ ዕድልን ፈጥሯል ነው ያሉት። የአርሶ አደሮች ተነሳሽነት እየጨመረ መምጣቱንም አንስተዋል።
🌨ከዝናብ ጥገኝነት ለመላቀቅ በመስኖ ልማት አርሶ አደሮች እንዲጠቀሙ በማድረግ የግብርና ዘርፉን ለማዘመን ተሠርቷልም ብለዋል።
በ2018 የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል መዘጋጀቱንም ገልጸዋል። በ261 ሺህ ሄክታር መሬት የመትከል ሥራ መጀመሩንም ተናግረዋል።
#አሚኮ_ዜና #ችግኝ_ተከላ #በአዊ_ ብሔረሰብ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ 🇪🇹
ዘጋቢ፦ ያየህ ፈንቴ
