በምሥራቅ ጎጃም ዞን የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች ወደሕዝብ ተመለሱ።

10

 

ደብረ ማርቆስ፡ ሰኔ 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን ባሶ ሊበን ወረዳ ወረዳ እና አካባቢው በትጥቅ ትግል በጫካ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ታጣቂዎች ከነትጥቃቸው የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።

የሰላም አማራጭ የተቀበሉት በወረዳው በረሃማ አካባቢዎች ታጥቆ ሲንቀሳቀስ የነበረው በእነሱ አጠራር የአብራጅት ብርጌድ ጦር አዛዥ ደህናሠው ሙሉቀን፣ የዘመቻ መምሪያ ኀላፊ የነበረው መዝናቸው ይሌ እና ሌሎችም ታጣቂዎች ናቸው።

የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎችን በአካባቢው ሕግ በማስከበር ላይ የማገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አዛዦች፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን እንዲሁም የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር አመራሮች እና የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

#አሚኮ #አሚኮዜና #ሰላም #ደብረማርቆስ #የሰላምአማራጭ #ኢትዮጵያ

Previous article“በሁሉም እሴቶቻችን የተስፋ አምባሳደሮች ሁኑ” መቅደስ ዳባ (ዶ.ር)